
#114መሳሪያ፤ በችግኝ ጣቢያ ከተባ ማካሄድ
114⸱Aጽንሰ-ሐሳብ
- የቡና ተክል ተባዮችን እና በሽታዎችን የመቋቋም ችሎታ ያሻሽላል፤
- የቡና ተክልን የአካባቢ ሙቀት መጠን መጨመር እና ድርቅን የመቋቋም ችሎታ ያሻሽላል፤
- የቡና ምርትን ይጨምራል፤
- የቡና ጥራትን ያሻሽላል፤
ከተባ ወይም ማጣበቅ ከተለያዩ እፅዋት የተውጣጡ ሁለት አካላት ማለትም መሰረተ ግንድ እና ፍሬ ሰጭ የዕፅዋት ክፍሎችን አንድ ላይ በማጣበቅ እንደ አንድ ተክል እንዲያድጉ የሚያደርግ የእፅዋት ማባዛት ዘዴ ነው። ዓላማው በአዲሱ ተክል ውስጥ የእያንዳንዱ ተክል ተፈላጊ ባህሪያት ማዋሃድ አንድ ማድረግ ነው።
መሰረተ ግንድ አዲስ የተገኘው ተክል መሰረት ነው። በተለምዶ የሚመረጠው በጥንካሬው፣ አካባቢን በሰፊው የመላመድ ችሎታ እና ለሰብል እድገት ተስማሚ ያልሆነ የአፈር ይዘት ፣ ተባዮች ወይም በሽታዎች፣ ድርቅ ወይም የአየር ንብረት ለውጦችን ጨምሮ የተለያዩ የባዮቲክ እና የአቢዮቲክ ምክንያት ሊፈጠር የሚችለውን ተፀዕኖዎች የመቋቋም ችሎታ ያለው ነው።
ፍሬ ሰጭአካል ወይም ሳዮን በመሰረተ ግንዱ ላይ የተከተበ ወይም የተጣበቀ ቡቃያ ወይም ቅርንጫፍ ነው። ከፍተኛ ምርት ወይም የላቀ ጥራት ካለው ጤናማ ተክል የተገኘ ነው።
ይህ አሰራር ገበሬዎች ደካማ ጥራት ያላቸውን ተክሎች እንዳያሳድጉ እና የበለጠ ተፈላጊ ወይም የላቀ ዝርያ ማልማት እንዲለምዱ ያስችላቸዋል። ምሳሌ፦ አረቢካ በሮቡስታ ወይም በአረቢካ በላይቤሪያ ላይ በመክተብ ወይም የተለያዩ በአረቢካ ዝርያዎችን በማጣመር ናቸው።
ችግኝ ከተባ ወይም ማጣበቅ መጀመሪያ አካባቢ ላይ የቡና ሥር ተባዮችን ኔማቶዶችን ለመቆጣጠር የሚያገለግል መሳሪያ ነበር። ሮቡስታ ኔማቶዶችን የሚቋቋም የቡና ዝርያ ዓይነት ነው። ስለሆነም በቡና ተከላ ቦታ ላይ ኔማቶድ በሚከሰትበት ጊዜ እንደ መሰረተ ግንድ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።
ሆኖም በኔማቶድ ያልተጠቃ መሆን ሲገባው የሮቡስታ ስር እድገት ከሌሎች የቡና ዝርያዎች በበለጠ የመስፋፋት እና ጠንካራ ይዘት ሲኖረው የበለጠ ጠቃሚ ነው። ይህም የአየር ንብረት ለውጥን የዝናብ እጥረት፣ ረዥም ድርቅ እና ከፍተኛ የአየር ሙቀት እንዲሁም ለም ያልሆነ ወይም ከባድ አፈር የመሳሰሉ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖዎችን ለመቋቋም ያስችላል።
114⸱Bከግምት ሊገቡ የሚገባቸው ጉዳዮች፦
የመክተብ ወይም የማጣበቅ ስራው በችግኝ ጣቢያ ውስጥ በዚህ ስራ የሰለጠነ ባለሙያ መከናወን አለበት። ባለሙያው ልምድ እያዳበረ በመጣ ቁጥር ውጤቱ የተሻለ ይሆናል። የችግኝ የመጣበቅ እድል በተሳካለ ሁኔታ እንዲያድግ ከፍተኛ ጥራት ያለው መሰረተ ግንድ እና ምርታማ እና ጥራት ያለው ፍሬ ሰጭ አካል እንዲጠቀሙ ይመከራል።
ሮቡስታ ዝርያ እንደ መሰረተ ግንድ የምንጠቀም ከሆነ በከፍታ ቦታ ቀዝቃዛ ዞኖች ከባህር ጠለል በላይ ከ1,200 ሜትር በላይ የእድገት ውስንነት ሊኖረው እንደሚችል በማሰብ አስፈላጊው ጥንቃቄ መደረግ አለበት። ምክንያቱም ሮቡስታ ቡና ሞቃታማና እርጥበት አዘል በሆኑ የአፍሪካ ቆላማ አካባቢዎች የለመደ በመሆኑ የተከተበው የቡና ተክል ልማት በከፍታ ቦታዎች ላይ አጥጋቢ እድገትና ምርታማነት ሊኖረው አልቻለም። ወጣቶች እና ሴቶች የከተባ ወይም የማጣበቅ ስራ በተሻለ ሙያዊ ብቃት እና በቡና እሴት ሰንሰለት ውስጥ እንዲሳተፉ እድል ይሰጣል።
የመጠቀሚያ ጊዜ፦
በችግኝ ጣቢያ ውስጥ ውጤታማ የከተባ ሂደት ከ45-50 ቀናት /1-2 ወራት በኋላ ሊጠናቀቅ ይችላል። የማሳ እድሳት ወይም አዲስ ተከላ ከሚካሄድበት ወቅት ጋር እንዲጣጣም የተከተቡ ተክሎች ለተከላ ወቅት ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የችግኝ ዝግጅታችን ጋር በተጣጣመ መልኩ መሆናቸውን ይኖርባቸዋል።
114⸱Cአተገባበር
ቁሳቁሶች
በተቻለ መጠን አንድ የሰለጠነ የችግኝ ጣቢያ ባለሙያ የችግኝ ከተባ ሂደት ቢያከናውን ይመከራል።
መሰረተ ግንድ ከሚከተሉት ባህሪዎች ሊኖሩት ይገባል።
- ለምሳሌ ፦እንደየ አካባቢው ሁኔታ የሚወሰንሆኖ ሮቡስታ አረቢካ ወይንም ሊበሪካ ሊሆኑ ይችላል።
- ከሳዮን ጋር ተኳሃኝነት፤ ብዙውን ጊዜ ስለዚያ በቂ መረጃ ከብሔራዊ የቡና ምርምር ተቋማት ወይም ከአካባቢው መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ሊገኝ ይችላል።
- ጠንካራ ሥሮች፤
- ተባዮችን ወይም በሽታዎችን መቋቋም። ኢንዶኔዥያ፡- ለምሳሌ ሮቡስታ ቢፒ 308 እንደ ኔማቶድ የሚቋቋም ዝርያ ሆኖ የተመረጠ ነው።
- ጠንካራ ግንድ፤
- የመሰረተ ግንድ ከሳዮኑ እኩል ወይም ትልቅ የሆነ ዲያሜትር ቢያንስ የመደበኛ እርሳስ መጠን ሊሆን ይገባል።
ፍሬ ሰጭ አካል የሚከተሉት ባህሪዎች ሊኖራቸው ይገባል።
- ለምሳሌ፦ አረብካ ወይም ሮቡስታ
- ከመሰረተ ግንዱ ጋር ተኳሃኝነት ያለው ። ይህ መረጃ ብዙውን ጊዜ ከብሔራዊ የቡና ምርምር ተቋማት ወይም ከአካባቢው መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ሊገኝ ይችላል።
- እንደ ከፍተኛ ምርት ወይም ጥራት ያሉ ተፈላጊ ባህሪያት፤
- ጤናማ እና ከተባይ ነፃ፤
- እንደዋና ግንድ የሚያድጉ ቅጥያዎች፣ በአቀባዊ ወደ ጎን እያደገ፤
- ጥሩ ቅርጽ፤
- መሰረተ ግንዱ ካለው ዲያሜትር ጋር እኩል የሆነ ወይም ያነሰ፣ ቢበዛ 1 ሴ.ሜ።
114⸱1መዘጋጀት
መሰረተ ግንድ እና ፍሬ ሰጭ አካላትን ችግኝ ማዘጋጀት፤
114⸱2አሰራር
ከተባ ወይም ማጣበቅ በሚካሄድበት ቀን የሚከናወን ሂደት;
የከተባ ስራ ችግኙ በጠዋት በቂ አየር እርጥበት ባለበት ሰዓት ቢሆን ይመረጣል።
114⸱3

114⸱4
የመሰረት ግንድ ያዘጋጁ፤
114⸱5
ፍሬ ሰጭ አካል (ለጋ ዛፎች) ያዘጋጁ።

114⸱6
ፍሬ ሰጭ አካል እና መሰረተ ግንዱን ያገናኙ:
የፓራፊልም ቴፕ ሲታሰር ሙሉ በሙሉ አየር እንዳገባ ያደርጋል፤ የፈንገስ እድገትን የሚያመጣ ውሃ (እርጥበት) ወደ ውስጥ እንዳይገባ ደርጋል፤ ከብዙ ከታቢዎች ጋር መስራት ከተቻለ አንድ ሰው በቀን የሚከትበው እና የሚያዘጋጀው የችግኝ ብዛት ይጨምራል።
114⸱7

ችግኝ ማባዣ መደብ አዲስ የተከተቡ ተክሎች ወደ ችግኝ ማሳደጊያ ቦታዎች ወይም ችግኝ መትከያ ማሳዎች ከመትከላቸው በፊት ቅድመ እድገትን እና እድገትን ወቀት በቂ እድገት እንዲኖራቸው ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራሉ። የችግኞቹ የመክተቢ ወቅት በጣም ደረቃማ እና ሙቅት፣ ወይም በጣም ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ በሚኖርበት ቢሆን ይመከራል።
114⸱8
114⸱9
114⸱10



ፍሬ ሰጭ አካል ከሞተ እና ምንም አይነት እድገትና አዲስ ቡቃያ ካላሳየ የከተባ ሂደት አልተሳካም ከተባው እንደገና ሊደገም ይገባል።
114⸱Dኢኮኖሚያዊ ጥቅሞ
የቡና ምርት መጨመር
ይህንን መሳሪያ መጠቀም የቡና ምርትን መጨመር እና ከፍተኛ ገቢ ያስገኛል።
የፀረ-ተባይ ወጪ ይቀንሳል
ይህ መሳሪያ ፀረ-ተባይ መድሃኒቶችን ፍላጎት ይቀንሳል። በዚህም ምክንያት በጊዜ ሂደት ወጪን ይቆጥባል።
ዝቅተኛ የማደሻ ወጪዎች
ይህ መሳሪያ የቡና ተክል ምርት የሚሰጥበትን ግዜ ሲያራዝም የዛፎችን የመፀደቅ ያሻሽላል። ይህም በሞተ ከዳ እንደገና ቡና በመትከል የምናወጣውን ወጭ የሚቀንስ ሲሆን በዚህም ምክንያት የረጅም ጊዜ የምርት ወጪዎችን ይቀንሳል።
114⸱Eአካባቢያዊ ጥቅሞች
አነስተኛ ፀረ-ተባዮች ያስፈልጋሉ
ይህ መሣሪያ የኬሚካል ፀረ-ተባዮች አስፈላጊነትን ይቀንሳል። ይህ የውሃ ብክለትን ይቀንሳል፣ ሥነ-ምህዳሩን ይጠብቃል፣ የአፈርን ሕይወት ያሻሽላል እንዲሁም ሀብቶችን ይቆጥባል።