ኮምፖስት

እንዲሁም ይገኛል ለ: ሆንዱራስ, ታንዛኒያ, ኢትዮጵያ, ኢንዶኔዢያ, ዩጋንዳ, ጉዋቲማላ

የሚመለከት:
አረቢካ, ሮብስታ

205⸱Aጽንሰ-ሐሳብ

  • የአፈር ቅርፅ እና የሕያዋን ቅሪት (ኦርጋኒክ ማተር) ያሻሽላል።
  • የአፈር ምርታማነት ያሻሽላል ።
  • የተክሎችን አመጋገብ ያሻሽላል።
  • የቡና ምርት ይጨምራል ።

ኮምፖስት ከማዕድን ማዳበሪያዎች በተጨማሪ ወይም ብቻውን ጥቅም ላይ ይውላል። የአፈር ለምነትን፣ የአፈር አወቃቀርንና የተክሎችን አመጋገብ ያሻሽላል፤ እንዲሁም በጊዜ ሂደት በአፈር ውስጥ ያለውን የተብላላ የሕያዋን ቅሪት ወይምሂሙስ ይዘት ይጨምራል።

ቀልዝ ወይም ኮምፖስት ኮምፖስቲንግ በሚባል ሂደት አማካኝነት ይመረታል። ኮምፖስቲንግ እና የሕያዋን ቅሪት (ኦርጋኒክ ማተር) አካል በረቂቅ ተሕዋስያን በሚብላላበት ባዮሎጂያዊ ሂደት ነው። ይህ ሁኔታ የሚከሰተው በኤሮቢክ (ኦክሲጅን) ሥር ሲሆንበቂ እርጥበትና የሙቀት መጠን ሊኖረው ይገባል። በመሆኑ ለአፈር አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ምንጭ የሆነና በውስጡ ባሉት ጠቃሚ ረቂቅ ተሕዋስያን አማካኝነት ወደ ምርት ሥርዓት ሕይወት የሚያመጣ አንድ ዓይነት ንጥረ ነገር እንዲሆን ያደርጋል።

የኮምፖስት አወቃቀሩ ለማዘጋጀት ከሚውለው ንጥረ ነገር ዓይነትና ብዛት ይለያያል። በመጀመሪያው ደረጃ የኮምፖስቲንግ ሂደት እንደ ቅጠል፣ ሣርና አትክልት ያሉ እርጥብ ንጥረ ነገሮችን በመከመር በጥቂት ወራት ውስጥ ቁሳቁሶቹ ወደ ኮምፖስት እስከሚበሰብሱ መጠበቅ ያስፈልጋል። ቡና በማምረት ሂደት ኮምፖስት ለማዘጋጀት ከሚቻልባቸው ዋና ዋና ንጥረ ነገሮች መካከል የቡና ገለባ እና ፍግ ሲሆኑ በተለይ የላም ወይም የዶሮ ፍግ ቢሆን ይመረጣል። ሌሎች ዕፅዋት ቁሳቁሶችንም በተለይ እንደ እርሻና የምግብ ማብሰያ ቤት ትርፍራፊ ያሉ መጠቀም ይቻላል። ኮምፖስቲንግ ሂደት 3-4 ወራት ይወስዳል.

ከጊዜ ብዛት ኮምፖስት በተለይዶ የምንጠቀምባቸውን ሰው ሰራሽ ማዳበሪያዎችን አጠቃቀም እንደሚያሻሽልና እነዚህን ማዳበሪያዎች የመጠቀም አስፈላጊነት እየቀነሰ እንደሚመጣ ይጠበቃል። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ኮምፖስት በአግባቡ መያዝ ከተቻለ ገንቢ ንጥረ ነገሮችን በአፈር ውስጥ በቀላሉ እንዳይተን እና እንዳጠፋ እንዲሁም የቡና ዛፍ በቀላሉ እንዲጠቀመው ስለሚያችለው ነው። ሰው ሰራሽ ማዳበሪያዎች ተፈላጊነታቸው ዝቅተኛ በመሆኑ ኦርጋኒክ ኮምፖስትን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲኖረውና የአፈር ጥራትና ጤንነት እንዲሻሻል ያደርጋል።

የአፈር አሠራሩን ሲሻሻል የቡና ተክል ሥሮች በቀላሉ ወደ ጥልቅ አፈር እንዲደርሱ ያደርጋል። በአሸዋማ አፈር ኮምፖስትና በዚህ ምክንያት የሚፈጠረው ሃሙስ የአሸዋው ቅንጣቶች አንድ ላይ ተያይዘው እርስ በእርስ እንዲጣበቁ ያደርጋል። ይህም በአፈርቅንጣት መካከል የቦታ (pores) መጠን ሲቀንስ ውሃ በአፈር ውስጥ ረዘም ላለ ጊዜ እንዲቆይ ያደርጋል። በሸክላ አፈር ውስጥ ኮምፖስት በሸክላ ቅንጣቶች ዙሪያ ተጨማሪ ቦታ (pores) በመያዝ እጽዋት ሥር ስርዓቶች የሚያስፈልጋቸውን ውሃ እና ንጥረ ነገር መድረስ እንዲችሉ, እንዲሁም አየር በአፈር ውስጥ መንቀሳቀስ ይችላል። በመሆኑም ከባድ የሸክላ አፈር እየቀለለና አሸዋማ አፈር እየከበደ ሲሄድ ኮምፖስት የተጨመረበት አፈር ለመስራት ማለትም ለማረስና ለመቆፈር ቀላል ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ኮምፖስት የተጨመረበት አፈር በቀላሉ በውኃና በነፋስ አማካኝነት እንዳይሸረሸር ይከላከላል። ይህ የሆነበት ምክንያት ውኃ ወደ አፈር በተሻለ ሁኔታ እንዲገባ ስለሚያስችልና ዝናቡ ወደ ጎርፍ እንዳድግ ስለማይችል ነው። ከኮምፖስት ጋር የተቀላቀለ አፈር ውሎ አድሮ የሕያዋን ቅሪት ወይምሂሙስ በነፋስ በቀላሉ ሊወሰድ አይችልም ።

በኮምፖስቲንግ ሂደት በአፈር ውስጥ ፋይቶፓቶጂን እንዲሁም ጎጂ ተክሎችና ዘሮች ይቀንሳሉ። ይህ ደግሞ ቡናን በቀጥታ ከማውጣት የተሻለ ነው ።

205⸱Bተንቀሳቃሽ ምስሉን ይመልከቱ፤

205⸱Cከግምት ሊገቡ የሚገባቸው ጉዳዮች፦

በአጠቃላይ, ሂደቱን ከመጀመሩ በፊት የአፈር ምርመራና ትንተና (ከመሳሪያ ጋር አያያዥ) መከናወን አለበት።.

በኮምፖስት አመራረት ሂደት የምንጠቀመው የዕፅዋትና የእንስሳት ትርፍራፊ መጠን በአፈር ውስጥ ካለው ንጥረ ነገር ጋር የተተያዘ ነው ። በኣጠቃላይ የቡና ገለባና እና የላም ፍግ በ3 ፡1 ድርሻ እንዲቀላቀል ይመከራል። የዶሮ ፍግ ጥቅም ላይ ከዋለ 4 ክፍሎች የቡና ገለባ እስከ 1 ክፍል ፍግ መጠቀም ይመከራል። እነዚህ መጠኖች በኮምፖስቲንግ ሂደት መጀመሪያ ላይ የካርቦን/ናይትሮጅን (C/N) መጠን 30/1 ገደማ እንዲሆን ለማድረግ ነው።

የመጨረሻውን ኮምፖስት ንጥረ ነገር ይዘት እና ጥራት ለማሳደግ እና በአፈር ምርመራ መሰረት ፎስፌት (P) እና ፖታሲየም (K) ለምሳሌ በአለት ፓውደር ወይም በእንቁላል ቅርፊት መልክ መጨመር ሊመከር ቢችል። ግብርና የአለት ዱቄት (ጅፕሰም) gypsum (calcium sulfate dihydrate CaSO4·2H2O) በመብላላት ወቅት የናይትሮጂን (N) ብክነትን መቀነስ እና ካልሲየም (Ca) እና ሰልፈር (S) መጨመር ወይም ማቅረብ ይመከራል። የአለት ዱቄት (ጅፕሰም) መጠን – ጥቅም ላይ ከዋለ – በክብደት ከፍተኛ እስከ 20% ሊደርስ ይችላል።

የኮምፖስቲንግ ሂደቱን ለማፋጠን እና የኮምፖሽኑን ጥራት ለማሻሻል, ባዮቻር (ወደ ተጨማሪ ማብራሪያ)  በክብደት እስከ 10% ድረስ ወደ ዝግጅቱ ሊጨመር ይችላል። የኮምፖስቲንግ ሂደት ጊዜ በ30% ቢቀንስ የሚፈለገው የማገላበጥ ቁጥር ይቀንሳል። ይህ የሆነበት ምክንያት ባዮቻር የኮምፖስቲንግ ክምችቱን በቂ አየር እንዲኖሮው ስለሚያሻሽል ነው ።

ሌላው የተሻሻለ የመበስበስ ዘዴ ቦካሺ የሚባለውን ተፈጥሮ ማዳበሪያ ማዘጋጀት ነው። ይህ ሂደት "ውጤታማ የሆኑ ረቂቅ ተሕዋስያን" በመቀላቀል የመበስበስ ሂደቱን ለማፋጠን ኮምፖስት ለማዘጋጀት በቀረበው ዕፅዋት እና ሌሎች ቁሳቁሶች ላይ የሚጨመርበት ሂደት ነው። ለተጨማሪ መረጃ የቦካሺ መሳሪያ (ወደ ተጨማሪ ማብራሪያ) ይመልከቱ።

አብሮ በመሥራት የሚገኝ እውነታ በቡድን ሆነው የሚሠሩ ገበሬዎች ብቻቸውን ከሚሠሩ ገበሬዎች ይልቅ ከፍተኛ ጥራት ያለው ኮምፖስት የማምረት አጋጣሚያቸው ሰፊ ነው ።

ጊዜ፦

አጠቃላይ የመብላላት እና የኮምፖስት ዝግጅት 3-4 ወራት ገደማ ይወስዳል። የኮምፖስት ምርት በደረቅ ወራት ጥሩ ተደርጎ ሊዘጋጅ ይገባል። ቡናው ከተሰበሰበና ከተዘጋጀ በኋላ በሚገኝው የቡና ገለባው ሳቆይ ወዲያውኑ መጠቀም የተሻለ ነው። ይህ ማለት ኮምፖስቱ ተዘጋጅቶ ለመጠቀም ዝግጁ ከሚሆንበት አራት ወራት አካባቢ በፊት ማለት ነው። ኮምፖስት በየአመቱ በቡና ማሳው ሊጨመር ይችላል። ማዳበሪያ በዓመት ውስጥ በተደጋጋሚ ከመጨመር እና ወጭ ከማውጣት ይልቅ አንድ ጊዜ ኮምፖስት ማዘጋጀትና መጠቀም ይችላል።

ኮምፖስት በየዓመቱ ጥቅም ላይ የሚውል ከሆነ አፈሩም እንዲሁ በየዓመቱም መመርመር ይኖርበታል። በዚህ መንገድ በንጥረ ነገሮች አወቃቀር ላይ ያለውን ለውጥ መከታተልና የምንጨምረውን ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ መጠን መቀነስ ይቻላል።

ኮምፖስትን ማዘጋጀትና ጥቅም ላይ ማዋል ትዕግሥት ይጠይቃል። በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ውጤቱ በግልጽ ላይታይ ይችላል ። ይሁን እንጂ ኮምፖስት በተከታታይ ጥቅም ላይ መዋሉ ለተከታታይ ዓመታት የሰብል ምርት ከፍ እንዲል ያደርጋል።

205⸱Dአተገባበር

ቁሳቁሶች

አስፈላጊውን ንጥረ ነገር መጠን ለመወሰን በዋናነት የአፈር ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል።
የምንጠቀምበት ቁሳቁሶች
በኮምፖስቲንግ ሂደት አማካኝነት የዝግጅት መጠን ክብደት ይቀንሳል። ለማዘጋጀት የሚሰበሰቡት ግብዓት ከመጨረሻው ከተዘጋጀው ተፈጥሮአዊ ኮምፖስት ክብደት የበለጠ ክብደት ያላቸው ለዚህ ነው።
ለ 1 ቶን (20 ኩ/ል) ለአጠቃቀም ዝግጁ ለሆነ ኮምፖስት ለማዘጋጀት፦

205⸱1መዘጋጀት

205⸱2ፕሮዳክሽን

ጥንቃቄ

የቁሳቁሶቹ ንብርብሮች በተገቢው መንገድ እንዲበከሉ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን በቅደም ተከተል ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው።

ጠቃሚ ምክር፡-

የኦርጋኒክ ንጥረ ነገሮች ንብርብሮች በሚቀመጡበት ወቅት ኮምፖስቱን በንጥረ ነገሮች የበለጸገ ለማድረግ ወይም አሲዱን ለመቆጣጠር እና የመበስበስ ንብርብር እንዲበሰብሱ ለማድረግ የትንሽ P (ፎስፎረስ) እና K (ፖታሽዬም) የሮክ ወይም አለት ዱቄት ወይም የተለመደ ላይም፣ አመድ ወይም የኬሚካል ማዳበሪያ (ዩሪያ) መካከለኛ ንብርብሮች መጠቀም ጥሩ ነው።

ጠቃሚ ምክር፡-

ክምሩን በእንጨት ፍሬም ወይም በሌላ ቁስ ማረጋጋት ይቻላል።

205⸱3

ጠቃሚ ምክር፡-

ርጥበቱን መጠን የእጅ ምርመራ ለመፈተሽ፦ የኮምፖስት የተወሰነ መጠን ወስደህ በእጅህ መጨበጥ። ናሙናው ቢሰበር (ቢፈርስ) ንጣፉን የበለጠ ማርጠብ አለብዎት። በጣቶችህ መካከል ጥቂት ጠብታዎች ብቅ ካሉ እርጥበቱ በቂ ነው። ውኃ በጣቶችህ መካከል ቢንጠባጠብ በጣም ብዙ ውሃ አለ። በዚህ ጊዜ ውኃ ማጠጣቱን አቁመህ ትንሽ እንዲደርቅ አድርግ።

205⸱4

ጠቃሚ ምክር፡-

ምንም እንኳ ኮምፖስት የሚመረተው በደረቅ ወራት ቢሆንምየመጨረሻው ንጣፍ በዝናብ ውኃ ሊከሰት የሚችለውን ብልሽት ለመከላከል ከዕፅዋት ቁሳቁስ ቢሠራ ይመረጣል። ከላይ ያለው ቀላል ተክል ይበልጥ ጥቅጥቅ ባለ ፍግ ከመዝጋት የተሻለ የመተንፈስችሎታ አለው።

205⸱5

205⸱6

ክምሩ መቸ ይገላበጣል

ጠቃሚ ምክር፡-

የሙቀቱን ለመሞከር የብረት ዘንግ ለመፈተሸ አንድ ባር 40 ሴሜ ወደ ክምር መሃል አስገባ እና እዚያ ለጥቂት ደቂቃዎች ይተውት። የብረቱ ዘንግ ሊሞቅና ጉዳት ሊደርስ ስለሚችል በእጅ ለመያዝ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። መያዝ ካልቻልክ ክምችቱን ማገላበጥ ይጠበቃል። በአንጻራዊ ሁኔታ ቀዝቃዛ ከሆነ (በእጅ መያዝ በጣም ቀላል ነው) ክምችቱን ይበልጥ ያረግበው።

ጠቃሚ ምክር፡-

በኮምፖስቲንግ ሂደት ከ3-4 ወራት ውስጥ በሆነ ወቅት ላይ ዝናብ ቢዘንብ፣ ንጥረ ነገሮች እንዳይታጠቡ ከተፈለገ ክምችቱን በፕላስቲክ ሊሸፈን ይገባል።

205⸱7

205⸱8አጠቃቀም፦

በአጠቃላይ እንደ አፈሩ የንጥረ ነገር ጥንቅር ፍላጎት ተግባራዊ መደረግ ያለበትን ትክክለኛ መጠን ለመወሰን የአፈር ምርመራ መደረግ አለበት።

አዲስ አዲስ የቡና ማሳ ለመተከል የምንጠቀም ከሆነ፦

  • በአዲሱ የቡና ማሳ ላይ ጉድጓዱ ሲያዘጋጅ 10 ቶን/ሄ/ር (200 ኩ/ል) እና ተጨማሪ 2 ቶን/ሄ/ር (40 ኩ/ል) ከተተከለ በኋላ ከላይ ላይ መጠቀም ይመከራል። በቡና ተክል ከ1-2 ኪሎ (ከ2 እስከ 3 ሊብራ) መሆን ይኖርበታል።
  • ኮምፖስቱ በእርሻው ውስጥ በሚቀመጥበት ጊዜ በፍጥነት በአፈር መሸፈን ይኖርበታል። ስለዚህ ፀሐይና ነፋስ አይጎዱትም። ናይትሮጅኑም ወደ ከባቢ አየር አያመልጥም። እንግዲህ ከማረሱ በፊት ወይም ደግሞ ሰብሉን ከመዝራቱ በፊት በእርሻው ላይ ኮምፖስት ማድረግ የተሻለ ነው።
  • በመስመር ለሚዘሩ ሰብሎች በመስመሩ ከዘሩ ጋር ሊቀመጥ ይችላል። በማዛመት ለሚተከል ሰብል ከችግኙ ጋር በጉድጓድ ውስጥ ማድረግ ይቻላል።

205⸱9

በነባር የቡና ማሳ ላይ የምንጠቀም ከሆነ፦

  • በነባር የቡና ማሳ ላይ ከ7 እስከ 8 ቶን/በሄ/ር (140-160 ኩ/ል/ሄ/ር) መሆን ይኖርበታል። ከዓት ወደ ዓመት በሂደት መጠኑን በመቀነስ ወደ 5 ቶን/በሄ/ር (100 ኩ/ል በሄ/ር ) መቀነስ ይቻላል። በእያንዳንዱ የቡና ተክል 250 ግራም (8 ግራም) መሆን ይኖርበታል።
  • ኮምፖስቱ በቡና ተክሎቹ መካከል ባለው አፈር ከላይ ሊወጣ ስለሚችል በማለዳ ወይም ከሰዓት በኋላ አመሻሹ ላይ መደረግ ይኖርበታል።
  • ኮምፖስቱ ከተጨመረ በኃላ በፍጥነት በአፈር መሸፈን አለበት። ስለዚህ ፀሐይና ንፋስ አይባክንም። ናይትሮጅንም ወደ ከባቢ አየር አይተንም። ከዚያም በአፈር ላይ በተደረገው ጥናት ውጤትን መሰረት አድርጎ በወጣው ምክረ ሓሳብ መሠረት በተለመዱ የማዕድን ማዳበሪያዎች ጋር መጨመር ይቻላል።

205⸱10

በቡና ችግኝ ጣቢያ፦

  • የቡና ችግኝ ለማዘጋጀት የምንጠቀም ከሆነ በጥንቅሩ ከ10-30% ድረስ አፈር ጋር በማቀላቀል ጥቅም ላይ ሊውል እስከ ይቻላል።

205⸱11

ሌሎች ሰብሎችን የምንጠቀም ከሆነ፦

  • እርግጥ ነው ኮምፖስት ከቡና ሰብል በተጨማሪ ለሌሎች ሰብሎችም ሊሰራ ይችላል።
  • በረድፍ ለሚተከሉ ሰብሎች፣ ለምሳሌ ለበቆሎ፣ ለማሽላ ወይም ለአትክልት፣ ኮምፖስቱ ከዘሮቹ ወይም ከቡቃያዎቹ ጋር በረድፍ ወይም በመስመር ማስቀመጥ ይቻላል።

ማከማቻ

ኮምፖስቱ ከዝግጅቱ በኋላ በቀጥታ ተግባራዊ መሆን ይኖርበታል።

ይህ የማይቻል ከሆነ፣ ኮምፖስቱ ከፀሐይና ከዝናብ የተጠበቀ፣ በቅጠሎች ወይም በአፈር የተሸፈነ፣ በፕላስቲክ ከተሸፈነ፣ ንጥረ ነገሮች ወደ ከባቢ አየር እንዳያመልጡ እና እንዳይባክን መደረግ አለበት።

ደረቅ እና እንደዚህ የተሸፈነ ሳይበላሽ ለበርካታ ሳምንታት ሊቀመጥ ይችላል።

205⸱Eኢኮኖሚያዊ ጥቅሞ

የማዳበሪያ ወጭ መቀነስ

ይህ መሳሪያ ሰው ሠራሽ ማዳበሪያዎችን ፍላጎት ይቀንሳል። በጊዜ ሂደት የግብዓት ወጪዎችን ይቆጥባል።

የቡና ምርት መጨመር

ይህንን መሳሪያ መጠቀም የቡና ምርትን መጨመር እና ከፍተኛ ገቢ ያስገኛል።

ቆሻሻን (ተረፈ ምርትን) እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል

የኢኮኖሚ አቅሙ በተለይ ለቦካሽ ዝግጅት አካል ሆነው የሚያገለግሉት ቆሻሻዎች (ተረፈ ምርቶችን) በእርሻ ላይ ወይም በአቅራቢያው ባሉ ቦታዎች ለምሳሌ፦ ከከብቶች ፍግ፣ ገለባ ወይም ከአካባቢው ማሳ የሚገኘውን እንጨት (ፍቅፋቂ ሰጋ ቶራ)። በተጨማሪም ቆሻሻን (ተረፈ ምርቶችን) በመጠቀም ይህ ቦካሽ ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ በማዋል የቆሻሻ መጣያ ወጪዎችን ለመቀነስ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

205⸱Fአካባቢያዊ ጥቅሞች

የሰው ሠራሽ ማዳበሪያዎችን መጠቀም መቀነስ

ይህ መሳሪያ በሰው ሠራሽ ማዳበሪያዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት ይቀንሳል። ይህም የካርቦን ልቀትን እና የውሃ ብክለትን ይቀንሳል። የአፈርን ለምነትን በማሻሻል ሀብቶችን ይቆጥባል።

ቆሻሻን (ተረፈ ምርትን) እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል፤

ሰርኩላር-ኢኮኖሚ ወይም የኡደት-ኢኮኖሜ ውስጥ ኦርጋኒክ ቆሻሻን (ተረፈ ምርትን) እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል የሚጣሉ ሀብቶችን ይቆጥባል። ይህ የአካባቢ ተፅእኖን፣ የካርቦን ልቀትን እና የውሃ ብክለትን ለመቀነስ ይረዳል።

የተሻለ የአፈር ሕይወት

ይህ መሳሪያ ለተክሎች እድገት አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆኑትን ንጥረ ነገር የሚያዘጋጁ እና ጤናማ ስነ-ምህዳርን እንዲኖረን የሚያደርጉ መሬት ውስጥ የሚኖሩ ትሎች (በአይን የማይታዩ ጥቃቅን ፍጥረታት) የአፈር ውስጥ እንዲኖሩ ያሻሽላል።

205⸱Gተጨማሪ ንባብ

205⸱Hአስተያየቶች