ተንቀሳቃሽ ቤት እና እሱ ውስጥ ከበቀል የሚያድጉ ተክልተኞች የተሳለ ምስል

እንዲሁም ይገኛል ለ: ሆንዱራስ, ብራዚል, ታንዛኒያ, ኢትዮጵያ, ኢንዶኔዢያ, ዩጋንዳ

የሚመለከት:
አረቢካ, ሮብስታ

102⸱Aጽንሰ-ሐሳብ

  • የቡና ተክል ድርቅን የመቋቋም አቅም ያሻሽላል።
  • የቡና ሞትን ይቀንሳል።
  • የቡና ምርትን ይጨምራል።

ትልቅ የቡና ችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም ችግኞቹ በሚያድጉበት ወቅት ረዘም ላለ ጊዜ በማቆየት የሚያስችል እና ወደ ማሳ ከመዛወራቸውና ከመትከላቸው በፊት በቂ የሥር እድገት እንዲኖራቸው ያደርጋል። በቂ እድገት ያላቸው ችግኞች ድርቅን በተሻለ ሁኔታ መቋቋም ይችላሉ።

በቅርብ ግዚያት ውስጥ ችግኝ ጣቢያ በቂ እድገት ሳይኖራቸው የተተከሉ የቡና ችግኖች ያለመፀደቅ ለአደጋ የተጋለጡ ሲሆኑ የተራዘመ ድርቅ በከፍተኛ ቁጥር የችግኝ መሞትን ሊያስከትል ይችላል። በመሆኑም በትልቅ ፕላስቲክ ከረጢት የተዘጋጀ ችግኝ የመፀደቅ ምጣኔ ከፍ ከማድረግ ባለፈ የችግኝ ሞት ማጣኔ እንዲቀንስ ያደርጋል።

ከተለመደው 20 ሴ.ሜ ካነሰ ይልቅ እስከ 28 ሴ.ሜ ፕላስቲክ ከረጢት ቁመት ሲኖረው ችግኞቹ ለተጨማሪ 5-6 ወራት ድረስ በችግኝ ጣቢያ ውስጥ እንዲቆዩና ሥሮቻቸው በበቂ ጠልቀው እንዲያድጉ ያደርጋል። በአጠቃላይ ረጅም ወራት እንዲቆይ ያደርጋል። ውሃ በማጠጣት ሥሮቻቸው ወደ ታች የረዘመ እድገት እንዲኖራቸው ያደርጋል።

በብራዚል የተደረገ የመፀደቅ ምጣኔ ሙከራ እንደሚያሳየው በችግኝ ጣቢያ አጭር ግዜ የቆዩ እና በአግባቡ ሳያድጉ የተተከሉ ችግኖች ከመጠን በላይ ያደጉ ችግኞች ጋር ሲነፃፀር የሞት መጠን በ 20 በመቶ ቀንሷል። በሙከራው እንደታየው በመጀመሪያ የእድገት ደረጃዎች እነዚህ ችግኞች ከሚያሳዩት ባህሪያት ከተለመዱት ችግኞች ጋር ሲነፃፀሩ የተሻለ ሆነው ታይተዋል። የእፅዋት ቁመት ፣ ግንድ ውፍረት፣ የመፀደቅ ምጣኔ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ቅርንጫፎች ብዛት፣ የመጀመሪያ ደረጃ ቅርንጫፎች ቁመት እና የአንጓ ብዛት የመሳሰሉት ከመጠን በላይ ያደጉ ችግኞች የመጀመሪያው ምርት ከመደበኛው ቡቃያ ከፍ ያለ ነው። (በታች ያሉትን ተጨማሪ ንባቦች ይመልከቱ)

102⸱Bከግምት ሊገቡ የሚገባቸው ጉዳዮች፦

የዚህ መሳሪያ አዋጭነት በአገር ውስጥ ገበያ ውስጥ ትላልቅ የፕላስቲክ ከረጢት በገበያ ላይ መገኘት የሚወሰን ሲሆን በተጨማሪም ፕላስቲክ ከረጢት ለመሙላት ተጨማሪ የሸክላ አፈር እና ኮምፖስት እንዲሁም ብስባሽ በበቂ ማግኘት ያስፈልጋል።

በትላልቅ የፕላስቲክ ከረጢት የሚዘጋጅ የቡና ችግኝ ወደ ተከላ ቦታ በሚጓጓዙበት ጊዜ ችግኞች ትልቅ እና ከባድ እንደሚሆኑ ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል።

ትልቅ ፕላስቲክ ከረጢቶች በተለይ በዘር ለሚዘጋጅ ችግኝ ይልቅ ማባዛት ይልቅ በቁርጥራጭ ችግኝ የማዘጋጀት ዘዴ መጀመሪያ ላይ የሥር አስተዳደግ ስርዓቱ ደካማ ስለሚሆን ጥቅም ላይ ቢውል የበለጠ አዋጭ ነው። ምክንያቱም ችግኞቹ በችግኝ ጣቢያ ውስጥ የቡና ችግኙ ስሮች ረዘም ላለ ጊዜ ጤናማ ሆነው ሊቆዩ ስለሚችሉ ለአርሶ አደሮች ረዘም ያለ የመትከያ ግዜ እንዲገኙ ዕድል ይሰጣቸዋል።

የመጠቀሚያ ጊዜ፦

በፕላስቲክ ከረጢቱ ከተዘራበት ጊዜ አንስቶ እስከ የሚተከልበት ጊዜ ድረስ በጥቅሉ11 ወራት ይወስዳል። በመሆኑም ዘሩ ወይም ችግኙ ዝናባማ ወቅት ከመጀመሩ 11 ወራት በፊት በፕላስቲክ ከረጢቱ መዘራትና መቆየት አለበት። የቡና ችግኝ ዝናብ መጀመሪያ ላይ ወደ መትከያ ማሳ በመዛወር ይተከላል።

በአጠቃላይ የአሰራር ሂደቱ በድርቅ ወራት በምንተገብርበት ግዜ የመፀደቅ ምጣኔ ከፍ ለማድረግ ረጅም

የፕላስቲክ ከረጢት እንደ የአፈር ክለት መከላከል የመሳሰሉት አሰራሮች ጋር በማቀናጀት መተግበር ይኖርበታል።

እንደ የተደራረበ (ጥቅጥቅ) ያለ መልች እና ጊዜያዊ ጥላ ዛፍ ፣ ህይወት ያለው ሽፋን ሰብል እና ተጓዳኝ ዛፎች መተግበሪያ መሳሪያዎችን ይመልከቱ።

102⸱Cአተገባበር

ቁሳቁሶች

102⸱1አሰራር

ጠቃሚ ምክር፡-

በዚህ መልኩ የተዘጋጀ እና ለተከላ የደረሰ ችግኝ ዝናብ በሚጀምርበት ወቅት ወደ ተከላ ቦታ በማዛወር መተከል ይኖርበታል።

102⸱2

ጠቃሚ ምክር፡-

በዚህ መልኩ የተዘጋጀ እና ለተከላ የደረሰ ችግኝ ዝናብ በሚጀምርበት ወቅት ወደ ተከላ ቦታ በማዛወር መተከል ይኖርበታል።

102⸱3

ጠቃሚ ምክር፡-

ከኬሚካል ማዳበሪያዎች በተጨማሪ እንደ ኮምፖስት ወይም ቦካሺ እንዲሁም ባዮቻር የመሳሰሉ የአፈርን ለምነት ለማስተካከል የሚጠቅሙ እና አዲስ ለተተከሉ የቡና ዛፎች አስፈላጊ የንጥረ ነገር አቅርቦትን ለማሻሻል የሚጠቅሙ የተለያዩ ኦርጋኒክ ማዳበሪያዎች አሉ።

102⸱4

102⸱Dኢኮኖሚያዊ ጥቅሞ

ዝቅተኛ የማደሻ ወጪዎች

ይህ መሳሪያ የቡና ተክል ምርት የሚሰጥበትን ግዜ ሲያራዝም የዛፎችን የመፀደቅ ያሻሽላል። ይህም በሞተ ከዳ እንደገና ቡና በመትከል የምናወጣውን ወጭ የሚቀንስ ሲሆን በዚህም ምክንያት የረጅም ጊዜ የምርት ወጪዎችን ይቀንሳል።

የቡና ምርት መጨመር

ይህንን መሳሪያ መጠቀም የቡና ምርትን መጨመር እና ከፍተኛ ገቢ ያስገኛል።

102⸱Fአስተያየቶች