#302የፕላስቲክ ጠርሙስ ጠብታ መስኖ አጠቃቀም
302⸱Aጽንሰ-ሐሳብ
- ውሃ ስርገትን ያሻሽላል።
- የአፈር እርጥበት ይዘት ያሻሽላል።
- የቡና ተክል ንጥረ ነገር አጠቃቀምን ያሳድጋል።
- የቡና ተክል መሞት ይቀንሳል።
- የቡና ምርት ይጨምራል።
- የውሃ ሃብትን በቁጠባ መጠቀም።
የጠርሙስ መስኖ ውሃ ከጠርሙሱ ወደ ተክሉ ሥሩ ቀስ በቀስ እንዲንጠባጠብ ያስችላል። ይህ መስኖ ዘዴን በቀላሉ ሊተገበር የሚችል ዘዴ መሆኑን መረዳት ይቻላል። የጠርሙስ መስኖ የሚተገበረው በተናጠል ለእንዳንዱ ተክል የሚተገበር ሲሆን ለምሳሌ፦ እንደ ችግኝ፣ ለትናንሽ ቡና እና በውስጡ ለሚተከሉ ቋሚ ጥላ ዛፎች (ተክሎች) እና ወይም አትክልት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ለሁሉም የአፈር ዓይነቶች እና ተዳፋት ተስማሚ ነው።
የሚያጋጥም ደረቅ ወቅት ለቡና ተክል በተለይም አዲስ ለተተከሉ ችግኞች ፈታኝ ነው። በመሆኑም ከመተከሉ በፊት እና ወዲያውኑ ውሃ በብዛት መጠጣት ይኖርበታል። የአየር ንብረት ለውጥ የሙቀት መጠንን በከፍተኛ ስለሚጨምር እና ደረቅ ወቅትን ስለሚያራዝም ከደረቅ ወቅት በተጨማሪ ለተክሉ ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል።
የጠርሙስ ጠብታ መስኖ የሚሠራው የተበሳ በውሃ የተሞላ የፕላስቲክ ጠርሙዝ ተገልብጦ ወደ ተክሉ አቅራቢያ አፈር በቅርብ ርቀት በመትከል ነው። ጥቅጥቅ ያለ አፈር ውሃው ወዲያውኑ ከጠርሙሱ እንዳይወጣ ይከላከላል። በምትኩ በእጽዋት ሥሮች አቅራቢያ ውሃው ወደ አፈር ውስጥ ቀስ ብሎ ዘልቆ ይገባል። አየር ያለማቋረጥ እና አረፋዎች ቀስ ቀስ ብለው ከአፈር ወደ ጠርሙሱ ሲገባ ተጨማሪ ውሃ ይለቃል።
ይህ ፅንሰ-ሀሳብ እንደ አፈሩ ቅንጣት መጠን ከጥቂት ሰዓታት እስከ ብዙ ቀናት ውስጥ ውሃን ወደ ተክሉ ስር ይሰጣል። በጠርሙሱ ውስጥ ውሃ እስካለ ድረስ ተክሉ የውሃ አቅርቦት አለው ማለት ነው።
የዚህ ዘዴ ዋና ዋና ጠቀሜታው ውጤታማነቱ ነው፡- ተክሉ በሚፈልገው ውሃ በሚጠቀምበት ቦታ ብቻ ስለሚወጣ የሚባክነው የለም ። በትነት እና በስርገት የሚባክን ውሃ መጠን ዝቅተኛ ነው።
በኡጋንዳ በሮቡስታ የቡና ችግኞች ላይ ባደረገው ጥናት መሰረት አርሶ አደሮች የጠርሙስ መስኖን በሚጠቀሙባቸው ቦታዎች የቡና ተክል የመፀደቅ ምጣኔ 100% የሚጠጋ መሆኑን ሪፖርት አድርገዋል። በተቃራኒ ይህ ዘዴ ባልተተገበረበት ቦታ ላይ 30% ብቻ የተርፉ መሆኑን አረጋግጠዋል። (ከታች ያሉትን ተጨማሪ ንባቦች ይመልከቱ)
302⸱Bከግምት ሊገቡ የሚገባቸው ጉዳዮች፦
በአጠቃላይ የአሰራር ሂደቱ እና ይህ የመስኖ ዘዴ በማደግ ላይ ያሉ ለወጣት ተክሎች ወይም ለትንሽ ማሳ ተስማሚ ነው። የጠርሙሶቹ ውሃ ባለቀ ግዜ ተደጋጋሚ መሙላት እና የሚፈላጉት ከፍተኛ ውሃ ስለማያሟሉ ለሰፋፊ ማሳዎች ወይም ለትላልቅ ዛፎች ተስማሚ አይደሉም።
የፕላስቲክ ጠርሙሶች በቀላሉ የሚገኙ እና ርካሽ ሀብቶች ሲሆኑ ወደ ቆሻሻ ከመጣሉ በፊት እንደገና እንድንጠቀም ያስችላል። ይሁን እንጂ ለእያንዳንዱ ችግኝ አንድ ጠርሙስ ስለሚያስፈልገው ሁሉንም በተወሰነ ግዜ ውሃ ለማጠጣት እና ለማዳረስ ብዙ የፕላስቲክ ጠርሙሶች ያስፈልጋሉ። ይህ በገጠር አካባቢ ሊያስቸግር ይችላል።
ሁሉም የፕላስቲክ ጠርሙሶች ጥቅም ላይ ከዋሉ በኋላ መሰብሰብ እና የአካባቢ እንዳበክሉ በአግባቡ መወገድ አለባቸው።
የአተገባበር ጊዜ፦
የጠርሙስ ጠብታ መስኖ በድርቅ እና አልፎ አልፎ ዝናብ በሚዘንብበት ጊዜ, በተለይም ችግኞችን በሚተክሉበት ጊዜ, ከነባር ተክሎች የበለጠ በተደጋጋሚ ውሃ ማጠጣት አስፈላጊ ነው።
302⸱Cአተገባበር
ቁሳቁሶች
302⸱1 የአሰራር ሂደት፦
አስፈላጊ ከሆነ በቀላሉ የሚሟሟ ማዳበሪያ በጠርሙሱ በመቀላቀል ወደ መስኖ ውሃ ውስጥ ማቀላቀል ይችላል።
302⸱2



ማሳሰቢያ ፦ ተክሉን እና ጠርሙሱን አዲስ በተቆረጡ የሙዝ ግንዶች ሊጠቀለሉ ይችላሉ። በመጀመሪያ እንደ ጉዝጓዝ በማድረግ በአትክልቱ ዙሪያ ያለውን በትነት የሚፈጠረውን የውሃ ብክነት ይቀንሳል። በሁለተኛ ደረጃ, ትኩስ የሙዝ ግንድ ብዙ ውሃ ስለሚይዝ በአፈር ውስጥ ተጨማሪ ውሃ ለመጨመር ይረዳል። በሶስተኛ ደረጃ ሲበሰብስ በአፈር ውስጥ ንጥረ ነገር ይጨምራሉ።
302⸱3
ሌሎች ለጉዝጓዝ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን መጠቀም ይቻላል። ነገር ግን ከቡና ግንድ 15 ሴ.ሜ/0.5 ጫማ ርቀት ላይ መቀመጥ አለባቸው።
302⸱Dኢኮኖሚያዊ ጥቅሞ
ዝቅተኛ የማደሻ ወጪዎች
ይህ መሳሪያ የቡና ተክል ምርት የሚሰጥበትን ግዜ ሲያራዝም የዛፎችን የመፀደቅ ያሻሽላል። ይህም በሞተ ከዳ እንደገና ቡና በመትከል የምናወጣውን ወጭ የሚቀንስ ሲሆን በዚህም ምክንያት የረጅም ጊዜ የምርት ወጪዎችን ይቀንሳል።
302⸱Eአካባቢያዊ ጥቅሞች
ውሃ ይቆጥባል፦
ይህ የመተግበሪያ መሳሪያ ውሃን እንደ አላቂ ሃብት በአግባቡ ቁጠባ በመጠቀም ያስችላል።