#206ቦካሺ
206⸱Aጽንሰ-ሐሳብ
- የአፈርን መዋቅር ያሻሽላል፣ የተፈጥሮ ማዳበሪያ (ኦርጋኒክ) ቁስ አካልን ይጨምራል፤
- የአፈርን ለምነትንና እድሜ ያሻሽላል፤
- የእፅዋትን ንጥረ-ነገር አመጋገብን ያሻሽላል፤ ለተክሎች የተመጣጠነ ምግብ
- አቅርቦትን እንዲጨምር ያሻሽላል፤
- የቡና ምርትን ያደርጋል፡፡
ቦካሺ ከተፈጥሮ ቁሳቁሶች ብስባሽ የሚዘጋጅ የተብላላ የአፈር ማዳበሪያ አይነት ነው። በቡና እርሻ ውስጥ አዘገጃጀቱ በተመለከተ ከፊል-ኤይሮቢክ የማብላላት ዘዴን በመጠቀም ከዕፅዋት ብስባሽና እና ከእንስሳት እዳሪ (ፍግ) ጋር እንደ ባክቴሪያ እና እርሾ ካሉ ጠቃሚ ረቂቅ ተሕዋስያን ጋር በማደባለቅ ተጣምሮ ይዘጋጃል፡፡
ምርቱ ለተክሎች በጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የተሞላ የተፈጥሮ (ኦርጋኒክ) የአፈር ማዳበሪያ ነው. ቦካሺ ከኦርጋኒክ- የብስባሽ (ኮምፖስት) የሚለየው በባዮኬሚካላዊ ሂደት የተጨመሩ ረቂቅ ተሕዋስያንን በማስገባት በማብላላት ዘዴን በመጠቀም የሚመረት ሲሆን በሚዘጋጅበት ጊዜ ቁሳቁሱን በአግባቡ እንዲብላላ ለመሸፈን የምንጠቀመው ቁስም ይለያል።ቦካሺ ለማምረት ወይም ለማዘጋጀት ከኦርጋኒክ- የብስባሽ (ኮምፖስት) ማዳበሪያ ያነሰ ጊዜ ይወስዳል።
በማብላላት ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሙቀት ይፈጠራል እና ይህንን ኦርጋኒክ (የተፈጥሮ) ቁስ አካል በማበስበስና በማብላላት ላይ ከሚሳተፉ የተለያዩ ፈንገሶች ከፍተኛ መጠን ያለው ማይሲሊየም (የሸረሪት ድር ወይም ቀጫጭን ክር የመሰሉ) ፈንገስ በላዩ ላይ ይስተዋላል፡፡ የዚህ ማዳበሪያ ዋነኛ ጠቀሜታ ለአፈር አስፈላጊ የሆኑ የማዕድን ንጥረ ነገሮችን በማቅረብ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ረቂቅ ተሕዋስያንን በማስተዋወቅ ብዝሃ ህይወትን ያሳድጋል። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ቦካሺን በአፈር ውስጥ መጠቀም ለተክሎች የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን እንደሚጨምር፣ የአፈርን ጥራት እና የምግብ ንጥረ ነገር ይዘትን እንደሚያሳድግ እና የሰብል ምርትን እንደሚጨምር ጥናቶች ያመለክታሉ።
ቦካሺ በአፈር ውስጥ ሲጨመር የአፈርን ኦርጋኒክ ቁስ አካል ከፍ ያደርገዋል፤ አካላዊ ኬሚካላዊ እና ስነህወታዊ ባህሪያቱን ያሻሽላል፡፡ እርጥበትን ይይዛል፣ ከመጠን በላይ ከሆነ ያስወግዳል እና በዚህም የአፈር መሸርሸር አደጋን ይቀንሳል፤ የአፈርን እርጥበት የመያዝ አቅም ያሻሽላል እና የአፈርን እፍጋት (ጥቅጥቅ ማለትን) ይቀንሳል፤ ይህ ማለት የተሻሻለ የአየር ዝውውር እና የተክሎች ሥሮቹ በቀላሉ እንዲያድጉ አካላዊ ብቅለትን ይቀንሳል፡፡
ቦካሺ ከፍተኛ የናይትሮጅን (ኤን) እና ፖታስየም (ኬ) ይዘት ያለው ሲሆን የተመጣጠነ ምግብን በተለይም ናይትሮጅን (ኤን)፣ ፎስፈረስ (ፒ)፣ ፖታሲየም (ኬ) እና ቦሮን (ቢ) እንዲሁም ማንጋኒዝ (ኤምኤን)፣ ዚንክ (ዜድ ዜን) እና መዳብ (ሲዩ) እና ሌሎችም እና የተመጣጠነ ምግብን በስርገት እንዳባክን (እንዳይቀንስ) ይረዳል።
የማብላላት ሂደት የአፈር ወለድ በሽታ አምጪ ተህዋስያንን እንዲሁም ጎጂ እፅዋትን እና ዘሮችን ይቀንሳል፡፡ ይህም የቡና ቅርፊትን (ጀንፈል) በቀጥታ ከመጠቀም ጋር ሲነፃፀር ጠቃሚ ነው፡፡ ስለዚህ ቦካሺ የማዕድን ማዳበሪያዎችን እና ፀረ-አረም መድኃኒቶችን የመጠቀም ፍላጎት ለመቀነስ፣ የምርት ወጪን ለመቀነስ፣ የቡና ምርትን ለመጨመር እና በአጠቃላይ የቡና ማምረቻ ወጭ ከሚገኝው ገቢ ጋር ያለውን ጥምርታ ሬሾ በማሳደግ የቡና ማምረት ስርዓቱን ወጪ ቆጣቢነት ለማድረግ ይረዳል፡፡
206⸱Bከግምት ሊገቡ የሚገባቸው ጉዳዮች፦
በአጠቃላይ የዝግጅቱ ሂደት ከመጀመሩ በፊት የአፈር ትንተና መደረግ አለበት።
በቦካሺ ምርት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውለው የእፅዋት ብስባሽ እና የእንስሳት እዳሪ (ፍግ) ጥምርታ የሚወሰነው በአፈር ውስጥ የሚኖረው ንጥረ-ነገር ውህደት ነው። በተለምዶ፣ 50/50 እኩል ክፍፍል ነው። ቦካሽ ለማዘጋጀት ከፍተኛ መጠን የቡና ቅርፊቶች (ጀንፈል) ካስገባን በትይዩ ፖታስየም ከፍተኛ ነው። ይህም በቡና ቅርፊት (ጀንፈል) በተፈጥሮው በከፍተኛ የፖታስየም ማዕድን የበለፀገ በመሆኑ ነው ።
ቦካሺ በሰው ሰራሽ ማዳበሪያዎች ጋር ሲነፃፀር በጣም ዝቅተኛ መጠን የማይክሮ ንጥረ ነገር ይዟል። በሌላ በኩል የአፈርን አካላዊ፣ ኬሚካላዊ እና ባዮሎጂያዊ ባህሪያት ስላለው በከፍተኛ ደረጃ የአፈር ለምነት የማሻሻል አቅም አለው። የቦካሺ ንጥረ ነገር ይዘት ጥቅም ላይ በሚውሉት ቁሳቁሶች መሰረት ያደረገ ሲሆን እና የእጽዋት ፍላጎቶችን ለማሟላት አስፈላጊ ከሆነ ከሰው ሰራሽ ማዳበሪያዎች ጋራ በመጠቀም የተክሎችን ፍላጎት ሊያሟሉ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፦ ቦካሽ ስናዘጋጅ የእንስሳት እዳሪ (ፍግ) እና ከቡና ገለባ (ጀንፈል) ከተዘጋጀ አብዛኛውን ጊዜ በቂ ናይትሮጅን (ኤን) እና ፖታሲየም (ኬ) አለው ነገር ግን ዝቅተኛ የፎስፈረስ (ፒ) መጠን ይኖረዋል ። ይህም ከሮክ (ከድንጋይ) ዱቄቶች ሰው ሰራሽ ወይም ተፈጥሯዊ የፎስፈረስ ምንጭ በመጨመር ሚዛናዊ የNPK ጥምርታ ለማግኘት ሊሻሻል ይችላል። ይህ ማሟያ የሚከናወነው በቦካሺ ዝግጅት ሂደት መጀመሪያ ላይ ነው፡፡
የአተገባበርጊዜ፦
በኋላ ቦካሺን ለማምረት ወይም ለማዘጋጀት ምርት ከተሰበሰበ በኃላ ቢሆን ይመከራል ምክንቱም በቂ የቡና ቅርፊቶች (ጀንፈል) የምናገኝበት አና ለመጠቀም የምንችልበት ወቅት በመሆኑ ነው። ይመከራል፡፡ በተጨማሪ ተክሉ የቡና ዛፎች ማቆጠቆጥ በሚጀምርበት ወቅት አጠቃቀሙ ስለሚድግ የቮካሽ ምርቱ አስቀድሞ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
206⸱Cአተገባበር
ማከማቻ
ቦካሺ በአጠቃላይ ከተዘጋጀ በኋላ ወዲያውኑ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡ የተመጣጠነ ምግብን በአግባቡ ለመጠቀም ከተመረተ በ6 ወራት ውስጥ እንዲጠቀሙበት ይመከራል፡፡
ቦካሺን ማከማቸት አስፈላጊ ከሆነ ከፀሀይ ብርሀን፣ ከነፋስ እና ከዝናብ የተጠበቀ በዝግ፣ ቀዝቃዛ እና በቂ የአየር ዝውውር በሚገኝበት ቦታ በፕላስቲክ ከረጢት ወይም ጆንያ ከረጢቶች ውስጥ ማስቀመጥ ጥሩ ነው፡፡ በትክክል ከተከማቸ ከ 1-2 ዓመታት ሊቆይ ይችላል፡፡
በጆንያ ከረጢት ውስጥ ባልተቀመጥ ወይም ባልተሸፈነ በባዶ ቦታ ክፍል ውስጥ ከተቀመጠ የማከማቻው ጊዜ ከ 3 ወር መብለጥ የለበትም፡፡
206⸱Dኢኮኖሚያዊ ጥቅሞ
የማዳበሪያ ወጭ መቀነስ
ይህ መሳሪያ ሰው ሠራሽ ማዳበሪያዎችን ፍላጎት ይቀንሳል። በጊዜ ሂደት የግብዓት ወጪዎችን ይቆጥባል።
የቡና ምርት መጨመር
ይህንን መሳሪያ መጠቀም የቡና ምርትን መጨመር እና ከፍተኛ ገቢ ያስገኛል።
ቆሻሻን (ተረፈ ምርትን) እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል
የኢኮኖሚ አቅሙ በተለይ ለቦካሽ ዝግጅት አካል ሆነው የሚያገለግሉት ቆሻሻዎች (ተረፈ ምርቶችን) በእርሻ ላይ ወይም በአቅራቢያው ባሉ ቦታዎች ለምሳሌ፦ ከከብቶች ፍግ፣ ገለባ ወይም ከአካባቢው ማሳ የሚገኘውን እንጨት (ፍቅፋቂ ሰጋ ቶራ)። በተጨማሪም ቆሻሻን (ተረፈ ምርቶችን) በመጠቀም ይህ ቦካሽ ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ በማዋል የቆሻሻ መጣያ ወጪዎችን ለመቀነስ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
206⸱Eአካባቢያዊ ጥቅሞች
የሰው ሠራሽ ማዳበሪያዎችን መጠቀም መቀነስ
ይህ መሳሪያ በሰው ሠራሽ ማዳበሪያዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት ይቀንሳል። ይህም የካርቦን ልቀትን እና የውሃ ብክለትን ይቀንሳል። የአፈርን ለምነትን በማሻሻል ሀብቶችን ይቆጥባል።
ቆሻሻን (ተረፈ ምርትን) እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል፤
ሰርኩላር-ኢኮኖሚ ወይም የኡደት-ኢኮኖሜ ውስጥ ኦርጋኒክ ቆሻሻን (ተረፈ ምርትን) እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል የሚጣሉ ሀብቶችን ይቆጥባል። ይህ የአካባቢ ተፅእኖን፣ የካርቦን ልቀትን እና የውሃ ብክለትን ለመቀነስ ይረዳል።
የተሻለ የአፈር ሕይወት
ይህ መሳሪያ ለተክሎች እድገት አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆኑትን ንጥረ ነገር የሚያዘጋጁ እና ጤናማ ስነ-ምህዳርን እንዲኖረን የሚያደርጉ መሬት ውስጥ የሚኖሩ ትሎች (በአይን የማይታዩ ጥቃቅን ፍጥረታት) የአፈር ውስጥ እንዲኖሩ ያሻሽላል።