#105ቡና ፍሬ ቦርቧሪ ማጥመጃ
105⸱Aጽንሰ-ሐሳብ
- ቡና ተክል ከተባይ ጥቃት መከላከል፤
- የቡና ምርታማነትን መጨመር
ቡና ፍሬ ቦርቧሪ ማጥመጃ ጠርሙስ በከፍተኛ ደረጃ ቡና ፍሬ ቦርቧሪ (CBB) የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ውጤታማ መተግበሪያ መሳሪያ ነው። በሳሙና የተበጠበጠ ውሃ ከአንፀባራቂ ፕላስቲክ ጠርሙስ (ሃይላንድ) ወይም በተመሳሳይ በኤታኖል የተሞላ እና ከሽቦ ወይም ከገመድ ማንጠልያ የተሰራ ነው። ኤታኖል ተባዩን ለመሳብ የሚጠቅም ሲሆን ፣ ውሃው ተባዩን በማጥመድ እንዳይወጣ ያደርጋል። ይህ ቴክኖሎጂ በዩጋንዳ ብሄራዊ ቡና ምርምር ድርጅት (NARO) የተገኘ ነው።
ቡና ፍሬ ቦርቧሪ በሃገራችን ቡና ተክሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከማድረሱም በላይ እና በሃገራችን ስፋት ተሰራጭቶ ሚገኝ ሲሆን በመላው ቡና አብቃይ ሃገራት ተሰራጭቶ የሚገኝ ጉዳት እያስከተለ የሚገኝ ተባይ ነው። በውጤቱም ተባዩ በ30-35% ምርት የሚቀንስ ሲሆን እና የጥራቱ በከፍተኛ ደረጃ በማጓደል መንገድ በቡና ንግድ ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ጉዳት እያስከተለ የሚገኝ ተባይ ነው።
እንስሳቲቱ ቡና ፍሬ ቦርቧሪ ጥንዚዛ ከቡና ፍሬው ጫፍ ጀምሮ ወደ ውስጡ ሰርስሮ በመግባት ውስጡን በመቦርቦር በዚያ ላይ እስከ 70 የሚደርስ እንቁላሎች ትጣራለች። ይህ ጥቃት ከአበባ ከፈነዳ በኃላ ስምንት ሳምንታት ጀምሮ እስከ ምርት እስከሚሰበሰብ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ሊከሰት ይችላል። የተፈለፈሉቱ እንቁላሎች በቡና ፍሬ ይመገባሉ። ይህ ቡና ፍሬ በቀላሉ እንዲወድቅ ወይም እንዲሰበር እና በባክቴሪያና በፈንገስ በቀላሉ በመግባት እንዲጠቃ ሊያደርግ ይችላል።
105⸱Bከግምት ሊገቡ የሚገባቸው ጉዳዮች፦
የቡና ፍሬ ቦርቧሪ ጥንዚዛ (CBB) ለመካላከል ማህበረሰብን በስፋት ማሳተፍ የሚጠይቅ እርምጃ ነው፣ ምክንያቱም ተባዩቹ ረጅም ርቀት ሊበሩ ይችላሉ። አንድ ገበሬ ቡና ፍሬ ቦርቧሪ (CBB) ማጥመጃ ጠርሙስ መጠቀሙ ሆኖም ሌሎች ካልተጠቀሙ በአጠቃላይ መከላከያው ውጤታማ አይሆንም።
በተጨማሪም ቡና ፍሬ ቦርቧሪ (CBB) ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመከላክ ከማጥመጃ ጠርሙስ በተጨማሪ መወሰድ ያለባቸው ሌሎች ተጎዳኝ እርምጃዎች አሉ።
- የአፈርለምነትበማሻሻልለምሳሌ፦ባዮቻር,ወይም መጠቀም፤
- ቡና ማሳ እና ተክሎችን በተከታታይ አሰሳ ማድረግ የተጎዱ ፍሬዎችን ለመለየት፤
- ፓይቶሳኒታሪ (ተክሉን በማፀዳት) ተግባራትን እንደ የተጎዱ ፍሬዎችን በማሰባሰብ እና መሬት ላይ የወደቁት የተጎዱ ፍሬዎች ከማሳ ማጽዳት ይኖራሉ። ተጎድተው የወደቁ ፍሬዎችን የተሰበሰቡ ፍሬዎች መቃጠል ወይም መቅበር እና እንዲሞቱ የሚያስፈልጉትን የCBB ወጭ እንቁላሎች መገደል አለባቸው።
- የደረቁና አላስፈላጊ ቅርንጫፎችን በመቆርጥ በማስወገድ አላስፈላጊ ቅርናጫፎችን ማስወገድ።
- በምርምር ተቋማት የተገኙ ጥላ ዛፎች መተከል የተለያ ዛፎች ተከላ በምርምር ተቋማት የተገኙ ጥላ ዛፎች መተከል የተለያ ዛፎች ተከላ።በጥላ ስር በምናለማበት የቡና ልማት ስርዓት እነዚህን ተባዮች የሚበሉ ወፎችን ሊስብ ይችላል። ነገር ግን የጥላ ዛፍ እንዳይበዛና እጅግ ጥላ እንዳይሆን እና ለተባዮች መራቢያ አመች እንዳይሆን መጠንቀቅ አለብን ።
የአተገባበርጊዜ፦
ማጥመጃወቹን በየግዜው ልንከታተላቸው ልንቆጥራቸው ይገባል። በዝናብ ወቅት መጀመሪያ መተከል ሲኖርባቸው በየ 2 ሳምንት ማጨብና እንደገና ሊሞሉ ይገባቸዋል። ጠርሙሶቹ ሲያረጁ ማስወገድ ይገባል።
105⸱Cአተገባበር
ቁሳቁሶች
ለ 1 ሀክታር:
105⸱1 የአሰራር ሂደት
105⸱2
105⸱3
በእያንዳንዱ ቡና ዛፍ ላይ ማጥማጃ ጠርሙሱን ማስቀመጥ አያስፈልግም። ቢያንስ በ30 ቡና ዛፎች ቢያንስ 1 ወጥመድ ማስቀመጥ ውጤታማ ያደርጋል። ሆኖም የወጥመዶች ቁጥር ቢበዛ የተሻለ ውጤታማ ያደርገናል።
105⸱4
105⸱Dኢኮኖሚያዊ ጥቅሞ
የፀረ-ተባይ ወጪ ይቀንሳል
ይህ መሳሪያ ፀረ-ተባይ መድሃኒቶችን ፍላጎት ይቀንሳል። በዚህም ምክንያት በጊዜ ሂደት ወጪን ይቆጥባል።
የኪሳራ ቅነሳ
ይህ መሳሪያ የቡና ምርትን እና ጥራት መቀነስን ሊያስከትል የሚቸለውን ኪሳር መከላከል ይረዳል።
105⸱Eአካባቢያዊ ጥቅሞች
አነስተኛ ፀረ-ተባዮች ያስፈልጋሉ
ይህ መሣሪያ የኬሚካል ፀረ-ተባዮች አስፈላጊነትን ይቀንሳል። ይህ የውሃ ብክለትን ይቀንሳል፣ ሥነ-ምህዳሩን ይጠብቃል፣ የአፈርን ሕይወት ያሻሽላል እንዲሁም ሀብቶችን ይቆጥባል።






