ሰው ዛፍ ለመትከል ጒድጓድ ሲለፍ የተሳሳተ ምስል

እንዲሁም ይገኛል ለ: ሆንዱራስ, ታንዛኒያ, ኢትዮጵያ, ኢንዶኔዢያ, ዩጋንዳ, ጉዋቲማላ

የሚመለከት:
አረቢካ, ሮብስታ

107⸱Aጽንሰ-ሐሳብ

  • የቡና ምርትን ያሳድጋል።
  • የቡና ዛፎችን ያድሳል።
  • የቡና ተክል ድርቅን የመቋቋም አቅም ያሻሽላል።
  • የተባይ እና የበሽታ ለሚያስከትሉት ጉዳት የመጋለጥ እድል ይቀንሳል፡፡

የቡና ማሳ ማደስ (በሞተ ከዳ ተከላ ማካሄድ) ማለት ያረጁ እና ምርታማ ያልሆኑ የቡና ዛፎችን በተለይም ከ20 ዓመት በላይ የሆናቸውን ነቅሎ በማስወገድ በቦታው አዳዲስ የቡና ችግኞችን መተካትን ያካትታል።

የቡና ተክል ከተተከለ ከሁለት ወይም ከሦስት ዓመት በኋላ ፍሬ ማፍራት የሚጀምር ሲሆን እስከ 25 እስከ 30 ዓመታት ድረስ ምርት መስጠቱን ይቀጥላል። እንደየ አካባቢያዊ ሁኔታ እስከ 40-50 ዓመታት ምርት መስጠቱን ሊቀጥል ይችላል። የቡና ተክል ከስድስት እስከ ስምንት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛው ምርት የሚሰጥበት ግዜ ነው። ከዚህ ጊዜ በኋላ ምርቱ ቀስ በቀስ እየቀነሰ ይሄዳል።

የቡና ተክል የምርታማነት ዘመናቸው ከጨረሱ በኋላ (አንዳንዶች ከ25-30 ዓመታት እንደየ አካባቢያዊ ሁኔታ ከ40-50 ዓመታት) በኃላ የቡና አምራች ገበሬዎች ቡናቸውን በአዲስ መተካት እንዳለባቸው በዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ይመክራሉ። በተጨማሪም የሥራ ጫና ለመቀነስ ፣ በምርታማ ዛፎች እና አዲስ በተተከሉ ዛፎች መካከል ያለውን ጤናማ ሚዛን ለመጠበቅ እና የአርሶ አደር ገቢ እንዳይቋጥ በየዓመቱ የማሳው የተወሰነ ክፍል ብቻ እንዲያድሱ ይመክራሉ።

ከቡና ዛፍ ዕድሜ በተጨማሪ በተባይ እና በበሽታዎች ከፍተኛ ጉዳት ክስትት የቡና ማሳው እድሳት እንዲደረግለት የሚያስገድድበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። የአየር ንብረት ለውጥም ማሳውን ማደስ ወይም በአዲስ ድርቅን ወይም በሽታዎችን የሚቋቋሙ ዝርያዎችን እንደገና ለመተካት በቂ ምክንያት ሊሆን ይችላል። በተወሰኑ የአየር ንብረት ለውጥ ሁኔታዎች ለመላመድና እና ጥሩ ምርት ለማስጠት የሚችሉ የቡና ዝርያዎች መተካትን ያጠቃልላል።

107⸱Bከግምት ሊገቡ የሚገባቸው ጉዳዮች፦

የቡና ማሳ (የተወሰነ ክፍል) ማደስ (በሞተ ከዳ ተከላ ማካሄድ) መጀመሪያ አካባቢ ከፍተኛ ወጭ የሚጠይቅ ሲሆን እና አጠቃላይ ለጊዜው ምርትን የሚቀንስበት ሁኔታ ይፈጠራል። ይሁን እንጂ ከሁለት እስከ አምስት ዓመታት በኋላ አዲስ የተተከሉ ቡናዎች ምርት መስጠት ሲጀምሩ ምርታማነቱ ቀደም ከነበረበት ይጨምራል ይህም ከፍተና ገቢ ያስገኛል። በተጨማሪም የቡና እድሳት የማሳውን የረጅም ጊዜ እና ዘላቂ ምርታማነት ያረጋግጣል።

የቡና ማሳ መልሶ መተካት (በሞተ ከዳ ተከላ ማካሄድ) ማሳውን ለማዘመን የአተካከል ስርዓቱን ለማሻሻል ዕድል ይሰጣል። ተጓዳኝ ዛፎችን መትከል፣ ወይም እንደ ጉዝጓዝ ወይም የሽፋን ሰብሎችን የመሳሰሉ አፈር ጥበቃ ዘዴዎችን ለመተግበር ያሉ ተግባራት ሊያቀናጅ ይችላል።

በተጨማሪም, አዲስ እና የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን ለማቀናጀት ዕድል ይሰጣል።

በተክል ምርት ለመጨመር እና ምርት እየሰጠ የሚቆይበትን ዕድሜ ለማራዘም በተከታታይ የቡና ዛፍ እድሳት ተግባራትን (link to Renovation tool) በተከታታይ ማከናወን እንዳለብን ይመከራል። ከሌሎች ጥሩ የተሻሻሉ የግብርና አሰራር ዘዴዎች ጋር ማቀናጀት እና መተግበር ይኖርብናል።

የአተገባበርጊዜ፦

የቡና ምርታማነት ከቀነሰ በኋላ የቡና ማሳ እድሳት (በሞተ ከዳ ተከላ ማካሄድ) መከናወን ይኖርበታል። ይህ ብዙውን ጊዜ ከ20 እስከ 25 ዓመት እንደ አካባቢው እስከ 40-50 ባለው ዓመታት ሊደርስ ይችላል።

መልሶ ተከላ የዝናብ ወቅት እንደጀመረ መከናወን ሲኖርበት ዝናብ ሳገባደብ መጠናቀቅ አለበት ።

ከመልሶ ተከላ በፊት አጭር የዕረፍት ጊዜ (ለምሳሌ 2–3 ወራት) መፍቀድ አፈር እንዲያገግም ይረዳል እና የተባዮችና የበሽታዎች አደጋን ያነሳል።

በተለይም በቡና ማሳው እስከ 80% የሚሆኑት የቡና ተክሎች ምርታማነት ላይ መገኘት ሲኖርባቸው የተቀሩት 20% የሚሆኑት የቡና ተክሎች ደግሞ በእድሳት እና በማገገሚያ ደረጃ ላይ መገኘት አለባቸው።

107⸱Cአተገባበር

ቁሳቁሶች

107⸱1አሰራር

107⸱2

107⸱3

107⸱4

ጠቃሚ ምክር፡-

በማሽነሪ የተዋበዙ አካባቢዎች ውስጥ፣ የአሮጌ ተክሎችን መውጣት፣ መሬቱን መዘጋጀት፣ መሬት መቆፈር ወይም ጉድለቶች መሥራት፣ እና ማስተካከያ መተግበሪያ በማሽነሪ ተደርጋል።

107⸱5

107⸱6

107⸱7

107⸱8

ጥንቃቄ

30% የበሰበሰ ኦርጋኒክ ቁስ ወይም ብስባሽ ወደ ተከላው ጉድጓድ ውስጥ መቀላቀል ይመከራል።

107⸱9

107⸱Dኢኮኖሚያዊ ጥቅሞ

የቡና ምርት መጨመር

ይህንን መሳሪያ መጠቀም የቡና ምርትን መጨመር እና ከፍተኛ ገቢ ያስገኛል።

የተሻሻለ የቡና ጥራት

ይህንን መሳሪያ መጠቀም ከፍተኛ የቡና ጥራት ሊያሻሽል እና ገቢ እንዲጨምር ያደርጋል።

የኪሳራ ቅነሳ

ይህ መሳሪያ የቡና ምርትን እና ጥራት መቀነስን ሊያስከትል የሚቸለውን ኪሳር መከላከል ይረዳል።

የሰው ጉልበት ወጪዎችን መቀነስ

ይህ መሳሪያ መጀመሪያ ላይ አንዳንድ ተጨማሪ ሥራዎች እና ቁሳቁሶችን ሊፈልግ እና ተጨማሪ ወጭ ሊያስከትል ይችላል። ይሁን እንጂ ከጊዜ በኋላ ጥቅሞቹ የሰው ኃይል ፍላጎቶችን በመቀነስ አጠቃላይ ወጪዎችን ይቀንሳል።

የማዳበሪያ ወጭ መቀነስ

ይህ መሳሪያ ሰው ሠራሽ ማዳበሪያዎችን ፍላጎት ይቀንሳል። በጊዜ ሂደት የግብዓት ወጪዎችን ይቆጥባል።

የፀረ-ተባይ ወጪ ይቀንሳል

ይህ መሳሪያ ፀረ-ተባይ መድሃኒቶችን ፍላጎት ይቀንሳል። በዚህም ምክንያት በጊዜ ሂደት ወጪን ይቆጥባል።

107⸱Eአካባቢያዊ ጥቅሞች

የሰው ሠራሽ ማዳበሪያዎችን መጠቀም መቀነስ

ይህ መሳሪያ በሰው ሠራሽ ማዳበሪያዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት ይቀንሳል። ይህም የካርቦን ልቀትን እና የውሃ ብክለትን ይቀንሳል። የአፈርን ለምነትን በማሻሻል ሀብቶችን ይቆጥባል።

አነስተኛ ፀረ-ተባዮች ያስፈልጋሉ

ይህ መሣሪያ የኬሚካል ፀረ-ተባዮች አስፈላጊነትን ይቀንሳል። ይህ የውሃ ብክለትን ይቀንሳል፣ ሥነ-ምህዳሩን ይጠብቃል፣ የአፈርን ሕይወት ያሻሽላል እንዲሁም ሀብቶችን ይቆጥባል።

የደን ጭፍጨፋን መከላከል

ይህ መፍትሔ ለቡና ልማት የሚሆን ተጨማሪ መሬት የመመንጠር አስፈላጊነትን ይቀንሳል። ይህም ለደን እና ለስነ-ምህዳሮቻቸው ጥበቃ አስተዋፅኦ ያደርጋል

107⸱Gአስተያየቶች