ማልች

እንዲሁም ይገኛል ለ: ሆንዱራስ, ታንዛኒያ, ኢትዮጵያ, ኢንዶኔዢያ, ዩጋንዳ, ጉዋቲማላ

የሚመለከት:
አረቢካ, ሮብስታ

203⸱Aጽንሰ-ሐሳብ

  • የአፈር እርጥበት እና የሙቀት መጠንን ያስተካክላል፤
  • የአፈር መሸርሸርን ይቀንሳል፤
  • የአረም እድገትን ያዳክማል፤
  • የአፈርን ለምነት እና ምርታማነትን ያሻሽላል፤
  • የአፈርን መዋቅር እና የብስባሽ መጠንን ያሻሽላል፤
  • የእፅዋትን አመጋገብ ያሻሽላል፤

ጉዝጓዝ በሰብል መስመር እና በዛፎች መካከል ያለውን አፈር ለመሸፈን የደረቁ ወይም የበሰበሱ የእፅዋት ቅሪቶች ንብርብር ነው። እንደ ደረቅ ሣር፣ ገለባ፣ አገዳ፣ ወይም የበሰበሱ ኦርጋኒክ ቁሶችን የመሳሰሉ ሁሉንም ዓይነት የእጽዋት ቁሳቁሶች መጠቀም ይቻላል።

ገላጣ እና ያልተጠበቀ አፈር በንፋስ እና በዝናብ ለመሸርሸር እና ለቀጥታ ፀሀይ መጋለጥ እና በመድረቅ ከፍተኛ የአፈር ውስጥ ሙቀት ሊያስከትል ይችላል። በነዚህ ምክንቶችም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች እየጨመረ ነው።

ጉዝጓዝ እነዚህን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖዎች ለመላመድ ይረዳል። መሬቱን በቀጥታ ከፀሀይ ጨረር እና ከዝናብ ተጽእኖ ይጠብቃል፣ የአፈር መሸርሸርን ለመቀነስ ይረዳል፣ እና የአፈርን እርጥበት እና ሙቀትን ይቀንሳል። የአረም እድገትን ያዳክማል እና የጉዝጓዝ የተጠቀምበት ቁስ ሲበሰብስ፣ በአፈር ውስጥ ንጥረ ነገሮችን በመቀላቀል የአፈርን አወቃቀር በረጅም ጊዜ በማሻሻል ለተክሎች የተመጣጠነ ምግብን አቅርቦትን ያሻሽላል። የጉዝጓዝ ቀጥተኛ ያልሆነ ጥቅም ተባዮችን እና በሽታዎችን መከሰት እና ክብደትን ይቀንሳል። በተለይም የአፈር ውስጥ አካባቢያዊ ሁኔታ በማሻሻል አፈር ወለድ በሽታ እና ተባይ የመቋቋም ችሎታውን ይጨምራል።

203⸱Bተንቀሳቃሽ ምስሉን ይመልከቱ፤

203⸱Cከግምት ሊገቡ የሚገባቸው ጉዳዮች፦

ለጉዝጓዝ የምንጠቀምባቸው ቁሳቁሶች አዳዲስ ተባዮችን እና የአረም ዘሮችን በቡና ማሳ ውስጥ ሊያመጡ ይችላሉ። በተመሳሳይ የቡና ገለባ ሁለቱንም ችግሮች ሊያመጡ ስለሚችሉ ባንጠቀምበት ይመረጣል።አፈር ለምነት ለማሻሻል የቡና ቅርፊቶችን ከመጠቀምዎ በፊት እንደ ኮምፖስት ወይም ቦካሺ ስናዘጋጅ በመበስበስ ወይም የመቡካት ሂደትን ማለፍ አለባቸው ። በዚህ መንገድ ሊከሰቱ የሚችሉ ኢንፌክሽኖች ምንም ጉዳት አያስከትልም።

በቡና ማሳ ውስጥ ከቁጥጥር ውጭ የጉዝጓዝ እፅዋት ድርብርብ እንዳፈጠር ዘር ሳያወጡ በፊት ተቆርጠው ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው።

እንደየአካባቢው ሁኔታ፣ በደረቁ ወቅት ጉዝጓዝ በአካባቢው የእሳት አደጋ መንስኤ ሊሆን ይችላል። በጉዝጓዝ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን እሳትን ለመከላከል፣ የቡና መሬት ማጽዳት ከቃጠሎ እንዳፈጠር ይረዳል። እንዲሁም እንደ ሲጋራ ወይም ክብሪት ያሉ እሳት የሚፈጥሩ ቁሶች ጉዝጓዝ በተደረገበት የቡና ማሳ ውስጥ ከመጣል መቆጠብ ይኖርብናል።

ይህን ችግር ለመፍታት ከተገለፀው ጉዝጓዝ የተሻለ በአማራጭነት የሽፋን ሰብሎችን (ሕይወት ያለው ጉዝጓዝ ነው። የሽፋን ሰብሎችን (ሕይወት ያለው ጉዝጓዝ) የራሳቸው በርካታ ልዩ ልዩ ጥቅሞች አሏቸው ፤ የአፈርን እና የቡና ዛፎችን ይከላከላሉ፤ ነገር ግን ከቡና ማሳ ስር (ውስጥ) ስለሚዘሩ ባዮማስን ለማምረት ተጨማሪ ቦታ አያስፈልጋቸውም። በተጨማሪም አንዳንድ የሽፋን ሰብሎችን (ሕይወት ያለው ጉዝጓዝ) ዝርያዎች ናይትሮጅንን ከአየር ላይ መሳብ እና ከአፈር ጋር በማዋሃድ ቡናውን በማዳበር በቀጥታ ይጠቅማሉ።

ነገር ግን፣ ተጨማሪ ጉዝጓዝ ሊሆን የሚችል ቁሳቁስ ካለ፣ ከላይ የተገለፀው ጉዝጓዝ የቡና ማሳ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖዎች ለመቋቋም ወይም ለመቀነስ የሚረዳ ተግባራዊ አሰራር ነው።

የምንጠቀምበት ጊዜ ፦ በዓመቱ ሙሉ ጉዝጓዝ ሊሆን የሚችል ቁሳቁስ የምናገኝ ከሆነ በማንኛውም ጊዜ ሊተገበር ይችላል። ይሁን እንጂ ትክክለኛው ወቅት ከዝናባማው ወቅት በፊት ወይም ወዲያውኑ ከ2-3 ዝናብ በኋላ የተሻለ ነው ። በዚህ መንገድ የዛፉ ሽፋን መጪውን የዝናብ ውሃ መያዝ እና መቆጠብ ይችላል።

203⸱Dአተገባበር

ቁሳቁሶች

ለጉዝጓዝነት የምንጠቀምባቸው ቁሶች ለምሳሌ ምድጃዎች ፣ ጭልፋዎች፣ ቅጠሎች ወይም ደረቅ ሳር ሊሆኑ ይችላሉ።

  • የበቆሎ እና የማሽላ አገዳ
  • አኩሪ አተር ቃርሚያ,
  • የሙዝ ቅጠል,
  • ግብጦ
  • ዝሆኔ ሳር
  • የወፍ አተር
  • ብራኬሪያ
  • ሳር
  • አጥላስ
  • ኮንታላር
  • ገረንግሬ (በወጣት / ሥጋዊ ደረጃ ላይ ጥቅም ላይ ከዋለ)……..ወዘተ።

203⸱1አሰራር

203⸱2

ጥንቃቄ

ጉዝጓዙ የቡናውን ግንድ እንዳይነካው እና ተክሉን እንዳያበሰብሰው ይጠንቀቁ። ይህ ጥንቃቄ ለምሳሌ ከመሬት በላይ ያለውን የቡናው ግንድ እንዳይበሰብስ ይረዳል እና ቡናውን ለማበስበስ እና ጉዳት ለማድረስ የጉዝጓዙን ቁሳቁስ እንደ መሸጋገሪያ ለመጠቀም የሚሞክሩትን ጉንዳኖች እና ሌሎች ጥገኛ ነፍሳትን ያስወግዳል።

203⸱3

የደረቁ እፅዋት በየወቅቱ ሊጠበቁ እና ሊታደሱ ይገባል።

203⸱Eኢኮኖሚያዊ ጥቅሞ

የሰው ጉልበት ወጪዎችን መቀነስ

ይህ መሳሪያ መጀመሪያ ላይ አንዳንድ ተጨማሪ ሥራዎች እና ቁሳቁሶችን ሊፈልግ እና ተጨማሪ ወጭ ሊያስከትል ይችላል። ይሁን እንጂ ከጊዜ በኋላ ጥቅሞቹ የሰው ኃይል ፍላጎቶችን በመቀነስ አጠቃላይ ወጪዎችን ይቀንሳል።

የማዳበሪያ ወጪ መቀነስ

ይህመሳሪያለተቀነባበረማዳበሪያዎችዝቅተኛፍላጎትእንዲኖርያስችላልእናስለዚህየግብአትወጪዎችንበጊዜሂደትይቆጥባል።

የአረም ማጥፊያ መድሃኒት ወጪ መቀነስ

ይህመሳሪያየፀረ-ተባይመድሃኒቶችንፍላጎትይቀንሳልእናስለዚህየግብአትወጪዎችንበጊዜሂደትይቆጥባል።

203⸱Fአካባቢያዊ ጥቅሞች

ዝቅተኛ የመስኖ ውሃ ፍላጎት

ይህመሣሪያበማምረትሂደትየውሃንትነትበመቀነስየውሃአጠቃቀምንያሻሽላል።

ዝቅተኛ ፀረ-አረም ፍላጎት

ይህመሣሪያየፀረ-አረምመድኃኒቶችንፍላጎትይቀንሳል።የአካባቢእናየውሃብክለትበመቀነስዘላቂየአፈርለምነትማሻሻልእናየአካባቢሃብትንይቆጥባል።

203⸱Hአስተያየቶች