#202የጎርፍ ፍጥነት መቀነሻ እና ማገጃ
202⸱Aጽንሰ-ሐሳብ
- የአፈር ክለት ወየይም መሸርሸርን ይቀንሳል።
- የውሃ ስርገትን ያሻሽላል።
- የአፈርን ዕርጥበት ሚዛን ይጠብቃል።
ቁልቁለታማ እና ተዳፋታማ ቦታዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና እየተቀያየረ ከሚፈጠረው ዝናብ ክስተት ምክንያት በሚፈጠር ከባድ ጎርፋና ጅረቶች እና የአፈር መሸርሸር የመጨመር እድል ሰፊ ነው። ቁልቁለታማ እና ተዳፋታማ ቦታዎች ላይ የጎርፍ ፍጥነት መቀነሻ እና ማገጃ መስራት የውሃ ፍሰቱን ያቀዘቅዘዋል። ይህም የውሃ ስርገትን ከመጨመሩም በላይ የአፈር መሸርሸር በመቀነስ እና የአፈር ውስጥ ንጥረ ነገሮችን እንዳይታጠቡ ያደርጋል።
የጎርፍየጎርፍፍጥነትመቀነሻእናማገጃ፦
- ምሉእ ግድቦች እና ውሃ መውረያ ቅንጣቶች፣ሰው ሰራሽ ግድቦች እና የውሃን ፍጥነት የሚቀንሱ መዋቅሮች፣
- በድንጋይ ወይም በእፅዋት ተሰርተው በሂደት በተዳፋታማ ቦታዎች እርከኖችን መፍጠር የሚችሉ፣
- ሰፋ ብለው ጥልቀት የሌላቸው፣ የእፅዋት የተሸፈኙ በማሳ መካከል ለውሃ ማፋሰሻ የሚሰሩ ቦዮችን ሊያካትቱ
ይችላሉ።
እነዚህ የጎርፍ ፍጥነት መቀነሻ እና ማገጃ ትርፍ ውሃን በመያዝ ውሃ ማቆያ ወይም ማስረጊዎች ገንዳ መፍጠር ይችላሉ። ይህም ውሃ ወደ መሬት ውስጥ ሰርጎ እንዲገባ እና የከርሰ ምድር ውሃን መጠን እንዲበለፀግ ያስችለዋል። በዚህ መንገድ በአንጻራዊነት ሁለቱንም ከመጠን በላይ ሆነ ከመጠን በታች ውሃ መጠን ክስተትን ወይም ችግርን በቀላሉ የምንፈታበት መንገድ ነው።
ተዳፋታማ ቦታዎች የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል እና የከርሰ ምድር ውሃን ለማበልፀግ በአማራጭነት ልንጠቀመው የምንችለው ተግባር በመስክ ላይ የዝናብ ውሃ ማስረጊያ ገንዳዎች ስራዎች ናቸው። ይሁን እንጂ ይህ አሰራር በአጠቃላይ ለድንገተኛ የጎርፍ ክስተቶች ለመከላከል እንጅ የረጅም ጊዜ መፍትሄ እንደማሆን ሊታወቅ ይገባል።
202⸱Bከግምት ሊገቡ የሚገባቸው ጉዳዮች፦
የአተገባበር ጊዜ (ወቅት)
የጎርፍ ፍጥነት መቀነሻ እና ማገጃ በማንኛውም ጊዜ ሊገነቡ ይችላሉ። የቡና ችግኝ ከመተከሉ በፊት ቢሰራ ቀላል እና በቡና ችግኞች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ይቀንሳል። ከዕፅዋት ጋር በማጣመር በሚሰራበት ወቅት የእጽዋት የእድገት ጊዜ ግምት ውስጥ መግባት አለበት። የጎርፍ ፍጥነት መቀነሻ እና ማገጃ በተለይ ከረዥም ድርቅ በኋላ እና ከባድ ዝናብ ሊዘንብ በሚችልበት ጊዜ ጠቀሜታቸው የጎላ ይሆናል።
202⸱Cአተገባበር
202⸱1አሰራር
ከ 30% በላይ ተዳፋታማ ቦታዎች፦
202⸱2
በእፅዋት/አትክልት የሚሰሩ የጎርፍ ፍጥነት መቀነሻ እና ማገጃ፦
እንደ ዝሆን ሳር፣ ቬቲቨር፣ የሎሚ ሣር ወይም የጀርመን አይሪስ ያሉ ለብዙ ዓመታት የሚቆዩ እና ሰፍተው የሚበቅሉ እፅዋት ህያው የጎርፍ መቀልበሻ በመሆን የምንጠቀምባቸው ናቸው። በዚህም የውሃ ፍሰትን ለመቀነስ፣ የአፈር መሸርሸርን ለመቀነስ ብሎም የጎርፍ አደጋን ለመቀነስ ይረዳሉ። በተጨማሪም የውሃ ውስጥ ስርገትን በማፋጠን የከርሰ ውሃ መጠንን ያበለፀጋሉ። በጎርፉ የመጣ ደለል አፈር ወይም የአፈር ቅንጣቶች በተሰሩ የጎርፍ ፍጥነት መቀነሻ እና ማገጃ ይጠራቀማሉ። በዚህም ወደ ጅረቶች የሚፈሰውን የፍሳሽ መጠን ይቀንሳል፤. ተዳፋታማነቱ እየጨመረ በሚመጣ ግዜ የጎርፍ ፍጥነት መቀነሻ እና ማገጃ ተቀራርበው መሰራት ሲኖርባቸው እርከን በተሰራባቸው የቡና ማሳዎች, እርከኖቹ እንዳይንሸራተቱ ለመከላከል በጠርዙ ላይ ማገጃ ወይም ህይወት ያላቸው የጎርፍ ፍጥነት መቀነሻ እና ማገጃ እነደ ሳሮች ዓይነት መተከል አለባቸው።

ከባድ ዝናብ ባለባቸው አካባቢዎች ከ 0.5 እስከ 5% ተዳፋት ባላቸው ቦታዎች የሚሰሩ ጎርፍ ፍጥነት መቀነሻ እና ማገጃዎች ሳሮች በመትከል መስራት ይመከራል። ይህ ማለት ቡናውን ለመትከል ምልክት የተደረገበት መስመር የጎርፍ ፍጥነት መቀነሻ እና ማገጃ ከሚተከለው ሳር በመጠኑ ዘንበል ማለት ይኖርበታል። ይህ ትክክለኛውን የውሃ ፍሳሽ ለማቀላጠፍ እና ውሃ እንዳይከማች ይከላከላል። በተመሳሳይ የውሃው ፍሰት ቀስ በማድረግ የአፈር መሸርሸርን ማስቀረት ይቻላል።
202⸱3
በቡና ማሳ ውስጥ ወይም በአቅራቢው ለሚያልፍ ጎርፍ፦
ሰው ሰራሽ ግድብ እና አነስተኛ የውሃ መቋቻ ጉድጓዶች መገንባት
202⸱Dኢኮኖሚያዊ ጥቅሞ
ዝቅተኛ የማደሻ ወጪዎች
ይህ መሳሪያ የቡና ተክል ምርት የሚሰጥበትን ግዜ ሲያራዝም የዛፎችን የመፀደቅ ያሻሽላል። ይህም በሞተ ከዳ እንደገና ቡና በመትከል የምናወጣውን ወጭ የሚቀንስ ሲሆን በዚህም ምክንያት የረጅም ጊዜ የምርት ወጪዎችን ይቀንሳል።
የቡና ምርት መጨመር
ይህንን መሳሪያ መጠቀም የቡና ምርትን መጨመር እና ከፍተኛ ገቢ ያስገኛል።
202⸱Eአካባቢያዊ ጥቅሞች
የተሻለ የአፈር ሕይወት
ይህ መሳሪያ ለተክሎች እድገት አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆኑትን ንጥረ ነገር የሚያዘጋጁ እና ጤናማ ስነ-ምህዳርን እንዲኖረን የሚያደርጉ መሬት ውስጥ የሚኖሩ ትሎች (በአይን የማይታዩ ጥቃቅን ፍጥረታት) የአፈር ውስጥ እንዲኖሩ ያሻሽላል።