#201በመስክ የዝናብ ውሃ ማስረጊያ ገንዳዎች
201⸱Aጽንሰ-ሐሳብ
- የአፈር ክለትን ይቀንሳል።
- የውሃ ስርገትን ያሻሽላል።
- ለቡና የአፈር ለምነትን ያሻሽላል።
- የቡና ምርት ይጨምራል።
- የቡና አለመፀደቅ ወይም መሞት ይቀንሳል።
- የአፈር ለምነት አና ምርታማነትን ያሻሽላል።
የዝናብ ውሃ ማስረጊያ ገንዳዎች በቡና ረድፎች መካከል የሚፈጠር ረባዳማ ቦታ እንደመሆናቸው መጠን ከቡና ማሳ የሚወጣውን የጎረፍ ውሃ መቀነስ እና ውሃን ለማከማቸት ያገለግላሉ። ውሃው በተሰሩት ትናንሽ ማስረጊያ ገንዳዎች ውስጥ ለብዙ ደቂቃዎች ሰዓታት እና ቀናት ይቆያል። ይህ ውሃው ወደ አፈር ውስጥ ስርጎ መግባት እና ለተክሎች ዝግጁ እንዲሆን ጊዜ ይሰጠዋል። በተጨማሪም የሚፈሰው የውሃ መጠን እና ፍጥነት ስለሚቀንስ የአፈር መሸርሸርን ይከላከላል። አፈሩ እንዳይታጠብ እና አፈሩ በመታጠብ የሚፈጠረውን የንጥረ ነገረ ብክነት በመቀነስ የቡና ተክሎች በቀላሉ ሊጠቀሙበት የሚችለውን የአፈር ለምነት ያሻሽላል። በመሆኑም በአፈር ውስጥ ያለው ብዝሃ- ህይወት ይጠበቃል።
መተግበሪያው ምንጊዜም ከረጅም ጊዜ የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ልምምዶች ማለትም እንደ ህይወት ባላቸው እፅዋት ሽፋን አያያዥ ፣ ጉዝጓዝ እና እንዲሁም የውሃ ማፍሰሻ ማገጃዎች ፣ እርከኖች ወይም ማስረጊያ ገንዳዎች ህይወት ባላቸው እፀዋት ሽፋን ጎን ለጎን በዝናብ ውሃ የተረፈ ውሃ ፍሰትን መቀነስ ያስችላል።
201⸱Bከግምት ሊገቡ የሚገባቸው ጉዳዮች፦
በቡና በመስመር መካከል ህይወት ባላቸው እፀዋት ሽፋን ወይም ጉዝጓዝ የመሳሰሉት የቡና ረድፎች መካከል ያለው አፈር እንዳይታጠብ አና ወደተቆፈረው የዝናብ ውሃ ማስረጊያ ገንዳዎች እንዳይገባ ይረዳል። የሽፋን ሰብሎች ለማደግ የተወሰነ ጊዜ ስለሚወስዱ ቀድሞ መትከል እና መሸፈን አለበት። በሜካናይዝድ የማምረት ሂደት የምንከተል ከሆነ ደረቃማ ወቅት እንዳለቀ ቢሰራ የመጀመሪያ ዝናብ እንደዘነበ የተቀላቀለ ዝርያዎች የሽፋን ሰብሎችን መዘራት አለብን።
ይሁንእንጂተፋሰሶችየሽፋንሰብሎችወይምጉዝጓዝሳይደረግመጠቀምይቻላል።በተዳፋታማቦታየዝናብውሃማስረጊያገንዳዎችከተፋሰሶችከቦይዎችጋርበማጣመርየዝናብውሃእንዲፈስማድረግይቻላል።በዘልምድየምንተገብረውበቡናግንድአካባቢእናዙሪያውንመቆፈርመጋቢሥሩንስለሚጎዳመቅረትአለበት።
የአተገባበር ጊዜ፦
የዝናብ ውሃ ማስረጊያ ገንዳዎች ዝናብ ከመዝነቡ ቀደም ብሎ መዘጋጀት ይኖርበታል። በተለይም ረዘም ያለ ድርቅ እና ጠንካራ ዝናብ ወቅት የአፈር መሸርሸር የሚዳረግ ሲሆን የውሃ ስርገት ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል።
201⸱Cአተገባበር
ቁሳቁሶች
201⸱1አሰራር








መደበኛ የመትከያ ርቀቶችን (የእፅዋት ብዛት 2000 የቡና ተክሎች በሄክታር) የሚጠቀሙ ከሆነ,ለእያንዳንዱ ሁለት የቡና ተክሎች አንድ የውሃ ጉድጓድ ለመሥራት ይመከራል።
201⸱2እቅድ
201⸱Dኢኮኖሚያዊ ጥቅሞ
ለዝቅተኛ መስኖ ወጪዎች ።
ይህ መሳሪያ የቡናው መስኖ ውሃ ፍላጎትን ስለሚያራዝም በመሆኑም ወጭ ይቀንሳል።
የቡና ምርት መጨመር
ይህንን መሳሪያ መጠቀም የቡና ምርትን መጨመር እና ከፍተኛ ገቢ ያስገኛል።
201⸱Eአካባቢያዊ ጥቅሞች
ውሃ ይቆጥባል፦
ይህ የመተግበሪያ መሳሪያ ውሃን እንደ አላቂ ሃብት በአግባቡ ቁጠባ በመጠቀም ያስችላል።
የተሻለ የአፈር ሕይወት
ይህ መሳሪያ ለተክሎች እድገት አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆኑትን ንጥረ ነገር የሚያዘጋጁ እና ጤናማ ስነ-ምህዳርን እንዲኖረን የሚያደርጉ መሬት ውስጥ የሚኖሩ ትሎች (በአይን የማይታዩ ጥቃቅን ፍጥረታት) የአፈር ውስጥ እንዲኖሩ ያሻሽላል።